Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የቆሬ ልጆች ትም​ህ​ርት።

1 አቤቱ፥ በጆ​ሮ​አ​ችን ሰማን፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዘ​መ​ና​ቸው በቀ​ድሞ ዘመን የሠ​ራ​ኸ​ውን ሥራ ነገ​ሩን።

2 እጅህ ጠላ​ትን አጠ​ፋች፥ እነ​ር​ሱ​ንም ተከ​ልህ፤ አሕ​ዛ​ብን አሠ​ቃ​የ​ኻ​ቸው፥ አሳ​ደ​ድ​ኻ​ቸ​ውም።

3 በጦ​ራ​ቸው ምድ​ርን አል​ወ​ረ​ሱም፥ ክን​ዳ​ቸ​ውም አላ​ዳ​ና​ቸ​ውም፤ ቀኝ​ህና ክን​ድህ የፊ​ት​ህም ብር​ሃን ነው እንጂ፤ ይቅር ብለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና።

4 አም​ላ​ኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያ​ዕ​ቆብ መድ​ኀ​ኒ​ትን ያዘ​ዝህ።

5 በአ​ንተ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሁሉ እን​ወ​ጋ​ቸ​ዋ​ለን፥ በስ​ም​ህም በላ​ያ​ችን የቆ​ሙ​ትን እና​ዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለን።

6 በቀ​ስቴ የም​ታ​መን አይ​ደ​ለ​ሁም፥ ጦሬም አያ​ድ​ነ​ኝም፤

7 አንተ ግን ከከ​በ​ቡን አዳ​ን​ኸን፥ የሚ​ጠ​ሉ​ን​ንም ሁሉ አሳ​ፈ​ር​ሃ​ቸው።

8 ሁል​ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ከ​ብ​ራ​ለን፥ ስም​ህ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም እና​መ​ሰ​ግ​ና​ለን።

9 አሁን ግን ጣል​ኸን፥ አሳ​ፈ​ር​ኸ​ንም፥ አም​ላ​ካ​ችን፥ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ችን ጋር አት​ወ​ጣም።

10 በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን ዘንድ ወደ ኋላ​ችን መለ​ስ​ኸን፥ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም ተነ​ጣ​ጠ​ቁን።

11 እንደ በጎች ሊበ​ሉን ሰጠ​ኸን፥ ወደ አሕ​ዛ​ብም በተ​ን​ኸን፥

12 ሕዝ​ብ​ህን ያለ ዋጋ ሰጠህ፥ ለእ​ል​ል​ታ​ች​ንም ብዛት የለ​ውም።

13 ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ችን ስድብ፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ንም ላሉ መሣ​ቂ​ያና መዘ​በቻ አደ​ረ​ግ​ኸን።

14 ለአ​ሕ​ዛብ ተረት፥ ለሕ​ዝ​ቡም የራስ መነ​ቅ​ነ​ቂያ አደ​ረ​ግ​ኸን።

15 እፍ​ረቴ ሁል​ጊዜ በፊቴ ነው፥ እፍ​ረት ፊቴን ሸፈ​ነኝ።

16 ከሚ​ሳ​ደ​ብና ከሚ​ላ​ገድ ቃል የተ​ነሣ፥ ከሚ​ከ​ብብ ጠላት ፊት የተ​ነሣ ነው።

17 ይህ ሁሉ በእኛ ላይ ደረሰ፥ አል​ረ​ሳ​ን​ህም፥ ኪዳ​ን​ህ​ንም አላ​ፈ​ረ​ስ​ንም።

18 ልባ​ች​ንም ወደ ኋላው አል​ተ​መ​ለ​ሰም፥ ፍለ​ጋ​ች​ንም ከመ​ን​ገ​ድህ ፈቀቅ አላ​ለም፤

19 በክፉ ስፍራ አዋ​ር​ደ​ኸ​ና​ልና፥ የሞት ጥላም ሰው​ሮ​ና​ልና፥

20 የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ስም ረስ​ተ​ንስ ቢሆን፥ እጃ​ች​ን​ንም ወደ ሌላ አም​ላክ አን​ሥ​ተ​ንስ ቢሆን፥

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን በተ​መ​ራ​መ​ረው ነበር! እርሱ ልባ​ችን የሰ​ወ​ረ​ውን ያው​ቃ​ልና።

22 ስለ እርሱ ሁል​ጊዜ ይገ​ድ​ሉ​ና​ልና፥ እን​ደ​ሚ​ታ​ረ​ዱም በጎች ሆነ​ናል።

23 አቤቱ፥ ንቃ፤ ለም​ንስ ትተ​ኛ​ለህ? ተነሥ፥ ለዘ​ወ​ት​ርም አት​ጣ​ለን።

24 ለም​ንስ ፊት​ህን ከእኛ ትመ​ል​ሳ​ለህ? መከ​ራ​ች​ን​ንና ችግ​ራ​ች​ን​ንስ ለምን ትረ​ሳ​ለህ?

25 ነፍ​ሳ​ችን በመ​ሬት ላይ ተጐ​ሳ​ቍ​ላ​ለ​ችና፥ ሆዳ​ች​ንም ወደ ምድር ተጣ​ብ​ቃ​ለ​ችና።

26 አቤቱ፥ ተነ​ሥና ርዳን፥ ስለ ስም​ህም ተቤ​ዥን።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos