Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “በመ​ን​ገድ በማ​ና​ቸ​ውም ዛፍ ላይ ወይም በመ​ሬት ላይ ከጫ​ጭ​ቶ​ችና ከእ​ን​ቍ​ላል ጋር እና​ቲቱ በእ​ነ​ዚህ ላይ ተቀ​ምጣ የወፍ ጎጆ ብታ​ገኝ እና​ቲ​ቱን ከጫ​ጭ​ቶ​ችዋ ጋር አት​ው​ሰድ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በመንገድ ስታልፍ፣ አንዲት ወፍ ጫጩቶቿን ወይም ዕንቍላሎቿን የታቀፈችበትን ጐጆ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ብታገኝ፣ እናቲቱን ከነጫጩቶቿ አትውሰድ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “በመንገድ ስትሄድ አንዲት ወፍ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ጫጩቶችዋንም ሆነ እንቁላሎችዋን ዐቅፋ የተቀመጠችበትን ጎጆ ብታገኝ፥ እናቲቱን ወፍ ከነጫጩቶችዋ አትውሰድ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “አንዲት ወፍ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ጫጩቶችዋንም ሆነ እንቊላሎችዋን ዐቅፋ የተቀመጠችበትን ጎጆ ብታገኝ፥ እናቲቱን ወፍ ከነጫጩቶችዋ አትውሰድ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በመንገድ ስትሄድ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ እናቲቱ በጫጩቶችዋ ወይም በእንቁላሎችዋ ላይ ተኝታ ሳለች የወፍ ጎጆ ብታገኝ፥ እናቲቱን ከጫጩቶዋ ጋር አትውሰድ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 22:6
7 Referencias Cruzadas  

አቤቱ ከወ​ን​ድሜ ከዔ​ሳው እጅ አድ​ነኝ፤ መጥቶ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋኝ፥ እና​ትን ከል​ጆ​ችዋ ጋር እን​ዳ​ያ​ጠፋ እኔ እፈ​ራ​ዋ​ለ​ሁና።


ከአ​ንተ ጋር ያሉ​ትን አራ​ዊት ሁሉ፥ ሥጋ ያላ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር አው​ጣ​ቸው፤ በም​ድ​ርም ላይ ብዙ፤ ተባዙ። ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት።”


ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኃጥኣን ምሕረት ግን አለመመጽወት ነው።


በሕ​ዝ​ብ​ህም መካ​ከል ጥፋት ይነ​ሣል፤ እና​ትም በል​ጆ​ችዋ ላይ በተ​ጣ​ለች ጊዜ የሰ​ል​ማን አለቃ ቤት​አ​ር​ብ​ኤ​ልን በጦ​ር​ነት ቀን እን​ዳ​ፈ​ረሰ፥ አም​ባ​ዎ​ችህ ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።


ላም፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ብት​ሆን እር​ስ​ዋ​ንና ልጅ​ዋን በአ​ንድ ቀን አት​ረዱ።


አም​ስት ወፎች በሁ​ለት ሻሚ መሐ​ለቅ ይሸጡ የለ​ምን? ከእ​ነ​ርሱ አን​ዲቱ ስን​ኳን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አት​ረ​ሳም።


“ሴት የወ​ንድ ልብስ አት​ል​በስ፤ ወን​ድም የሴት ልብስ አይ​ል​በስ፤ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos