Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የዳ​ዊት ትም​ህ​ርት መዝ​ሙር።

1 ኀጢ​አ​ታ​ቸው የተ​ተ​ወ​ላ​ቸው፥ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያል​ቈ​ጠ​ረ​ባ​ቸው ብፁ​ዓን ናቸው።

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ሉን የማ​ይ​ቈ​ጥ​ር​በት በል​ቡም ሽን​ገላ የሌ​ለ​በት ሰው ብፁዕ ነው።

3 ሁል​ጊዜ ከመ​ጮኼ የተ​ነሣ ዝም ብያ​ለ​ሁና አጥ​ን​ቶቼ አረጁ፤

4 በቀ​ንና በሌ​ሊት እጅህ ከብ​ዳ​ብ​ኛ​ለ​ችና፥ እሾህ በወ​ጋኝ ጊዜ ወደ ጕስ​ቍ​ልና ተመ​ለ​ስሁ።

5 ኀጢ​አ​ቴን ነገ​ርሁ፤ በደ​ሌ​ንም አል​ሸ​ሸ​ግ​ሁም፤ ስለ ኀጢ​አቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሴን እከ​ስ​ሳ​ለሁ አልሁ፤ አን​ተም የል​ቤን ሽን​ገላ ተው​ልኝ።

6 ስለ​ዚህ ጻድቅ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይጸ​ል​ያል፤ ነገር ግን ብዙ የጥ​ፋት ውኃ ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ብም።

7 አንተ ካገ​ኘ​ችኝ ከዚች መከ​ራዬ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ ነህ፥ ከከ​በ​ቡ​ኝም ታድ​ነኝ ዘንድ ደስ​ታዬ ነህ።

8 አስ​ተ​ም​ር​ሃ​ለሁ፥ በም​ት​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ አጸ​ና​ሃ​ለሁ። ዐይ​ኖ​ቼን በአ​ንተ ላይ አጸ​ና​ለሁ።

9 ወደ አንተ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርቡ በል​ባ​ብና በል​ጓም ጉን​ጫ​ቸ​ውን እን​ደ​ሚ​ለ​ጕ​ሙ​አ​ቸው፥ ልብ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው እንደ ፈረ​ስና እንደ በቅሎ አት​ሁኑ።

10 የኃ​ጥ​ኣን መቅ​ሠ​ፍ​ታ​ቸው ብዙ ነው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ታ​መ​ኑ​ትን ግን ይቅ​ርታ ይከ​ባ​ቸ​ዋል።

11 ጻድ​ቃን ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጉ፤ ልባ​ች​ሁም የቀና ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ተመኩ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos