የወርቁና የብሩ ዕቃዎች ሁሉ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነዚህንም ሁሉ ሲሳብሳር ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱ ምርኮኞች ጋር ወሰደ።
ዕዝራ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከሮሃልያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጎዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከሠራያ፣ ከረዕላያ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከመሴፋር፣ ከበጉዋይ፣ ከሬሁም፣ ከበዓና ጋራ ነበር። የተመለሱት የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዔላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከቢልሻን፥ ከሚስፋር፥ ከቢግዋይ፥ ከሬሁምና፥ ከባዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለተመለሱትም ስደተኞች መሪዎች ሆነው የመጡት ዘሩባቤል፥ ኢያሱ፥ ነህምያ፥ ሠራያ፥ ረዔላያ፥ መርዶክዮስ፥ ቢልሻን፥ ሚስፓር፥ ቢግዋይ፥ ሬሁምና በዓና ተብለው የሚጠሩት ነበሩ። ከእያንዳንዱ እስራኤላዊ ጐሣ በመሰባሰብ ወደ ሀገር የተመለሱትም ስደተኞች ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዕላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጉዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ |
የወርቁና የብሩ ዕቃዎች ሁሉ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነዚህንም ሁሉ ሲሳብሳር ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱ ምርኮኞች ጋር ወሰደ።
የፋርስ ንጉሥ ቂሮስም የመዝገብ ሐላፊ በነበረው በሚትሪዳጡ እጅ አወጣቸው፤ ለይሁዳም መስፍን ለሲሳብሳር ቈጠራቸው።
የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ፥ ወንድሞቹም ካህናቱ፥ የሰላትያልም ልጅ ዘሩባቤል፥ ወንድሞቹም ተነሥተው በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡበት ዘንድ የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።
ዘሩባቤልና ኢያሱም፥ የቀሩትም የእስራኤል አባቶች ቤቶች አለቆች፥ “የአምላካችንን ቤት መሥራት ለእኛና ለእናንተ አይደለም፤ እኛ ራሳችን ግን የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዳዘዘን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ቤት እንሠራለን” አሉአቸው።
በዚያን ጊዜም የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸውም የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
በንጉሡ በአርተሰስታ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የወጡ የአባቶች ቤቶች አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ትውልዳቸውም ይህ ነው፤
እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፤ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።
ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ከረዓምያ፥ ከሄሜኔስ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበልሰማ፥ ከሚስፌሬት፥ ከዕዝራ፥ ከበጉዋይ፥ ከነሑም፥ ከበዓና፥ ከመስፈር ጋር መጡ። ከእስራኤልም ሕዝብ የወንዶች ቍጥር ይህ ነው፥
በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ አለቃ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤል፥ ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦
የሰላትያልም ልጅ ዘሩባቤል፥ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ድምፅ የነቢዩንም የሐጌን ቃል፥ አምላካቸው እግዚአብሔር እንደ ላከው ሁሉ ሰሙ፣ ሕዝቡም በእግዚአብሔር ፊት ፈሩ።
እግዚአብሔርም የይሁዳን አለቃ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፥ የታላቁንም ካህን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስ፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አስነሣ፣ በንጉሡም በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በሀያ አራተኛው ቀን መጡ፥ የአምላካቸውንም የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤት ሠሩ።
አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፥ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱና ሥሩ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።