Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ መን​ግ​ሥት ከእኔ ጋር ከባ​ቢ​ሎን የወጡ የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውም ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከባቢሎን ዐብረውኝ የወጡት የየቤተ ሰቡ አለቆችና ዐብረዋቸው የተመዘገቡት እነዚህ ናቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በንጉሡ በአርጤክስስ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የወጡ የአባቶች አለቆች እነዚህ ናቸው ትውልዳቸውም ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የተመለሱት የቤተሰብ አለቆች በየትውልዳቸው እንደሚከተለው ነው፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በንጉሡ በአርጤክስስ መንግሥት ከእኔ ጋር ከባቢሎን የወጡ የአባቶች ቤቶች አለቆች እነዚህ ናቸው። ትውልዳቸውም ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 8:1
16 Referencias Cruzadas  

እነ​ዚ​ህም ደግሞ በን​ጉሡ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ዶቅ በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በሌ​ዋ​ው​ያ​ንና በካ​ህ​ናት አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት፥ ታላ​ላ​ቆች እንደ ታና​ናሽ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


ወን​ድ​ሞ​ቹም ጽኑ​ዓን የነ​በ​ሩት የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉ​ሡም ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሁሉና በን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ሁሉ በሮ​ቤ​ላ​ው​ያ​ንና በጋ​ዳ​ው​ያን፥ በም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ላይ ሹሞች አደ​ረ​ጋ​ቸው።


መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ እስከ በኣል ድረስ በእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች ዙሪያ ነበሩ። መቀ​መ​ጫ​ቸ​ውና ድር​ሻ​ቸ​ውም ይህ ነበረ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ወደ ባቢ​ሎን ከተ​ማ​ረኩ በኋላ፥ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ተቈ​ጠሩ፤ እነ​ሆም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።


እነ​ዚህ ከሌ​ዋ​ው​ያን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው አለ​ቆች ነበሩ። እነ​ዚ​ህም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይቀ​መጡ ነበር።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች በሰ​ልፍ ጽኑ​ዓ​ንና ኀያ​ላን የሆኑ ሁሉ ቍጥ​ራ​ቸው ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበረ።


የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት ይወጡ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሳ​ቸ​ውን ያነ​ሣ​ሣው ሁሉ ተነሡ።


ከዘ​ሩ​ባ​ቤል፥ ከኢ​ያሱ፥ ከነ​ህ​ምያ፥ ከሠ​ራያ፥ ከሮ​ሃ​ልያ፥ ከመ​ር​ዶ​ክ​ዮስ፥ ከበ​ላ​ሳን፥ ከመ​ሴ​ፋር፥ ከበ​ጎ​ዋይ፥ ከሬ​ሁም፥ ከበ​ዓና ጋር መጡ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤


የፋ​ሮስ ልጆች ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት።


እነ​ዚህ በት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አል​ተ​ገ​ኘም፤ ከክ​ህ​ነ​ትም ተከ​ለ​ከሉ።


በመ​ን​ግ​ሥ​ቴም ውስጥ ካሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከካ​ህ​ና​ቱና ከሌ​ዋ​ው​ያኑ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሄድ ዘንድ የሚ​ወ​ድድ ሁሉ ከአ​ንተ ጋር እን​ዲ​ሄድ አዝ​ዣ​ለሁ።


በን​ጉሡ ፊት በሚ​መ​ክ​ሩ​ትም፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም፥ በን​ጉሡ አለ​ቆች ሁሉ ፊት በእኔ ላይ ምሕ​ረ​ቱን ላከ። እኔም በእኔ ላይ ባለ​ችው በአ​ም​ላኬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በረ​ታሁ፤ ከእ​ኔም ጋራ ይወጡ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆ​ቹን ሰበ​ሰ​ብሁ።


ይህም ዕዝራ ከባ​ቢ​ሎን ወጣ፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የሰ​ጠ​ውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአ​ም​ላ​ኩም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና ንጉሡ ያሻ​ውን ሁሉ ሰጠው።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከካ​ህ​ና​ቱም፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከበ​ረ​ኞ​ቹም፥ ከና​ታ​ኒ​ምም በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ዐያ​ሌ​ዎች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ።


ከፊ​ን​ሐስ ልጆች ጌር​ሶም፥ ከኢ​ታ​ምር ልጆች ዳን​ኤል፥ ከዳ​ዊት ልጆች ሐጡስ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos