ዕዝራ 2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ዝርዝር 1 የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። 2 ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዔላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከቢልሻን፥ ከሚስፋር፥ ከቢግዋይ፥ ከሬሁምና፥ ከባዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው። 3 የፓርዖሽ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት። 4 የሸፋጥያ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። 5 የአራሕ ልጆች፥ ሰባት መቶ ሰባ አምስት። 6 የፓሐት ሞዓብ ልጆች የኢያሱ ዮአብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዐሥራ ሁለት። 7 የዔላም ልጆች፥ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 8 የዛቱ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት። 9 የዘካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ። 10 የባኒ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት። 11 የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ሦስት። 12 የዓዝጋድ ልጆች፥ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሀያ ሁለት። 13 የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት። 14 የቢግዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አምሳ ስድስት። 15 የዓዲን ልጆች፥ አራት መቶ አምሳ አራት። 16 ከሕዝቅያ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት። 17 የቤፃይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሃያ ሦስት። 18 የዮራ ልጆች፥ መቶ ዐሥራ ሁለት። 19 የሐሹም ልጆች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት። 20 የጊባር ልጆች፥ ዘጠና አምስት። 21 የቤተልሔም ልጆች፥ መቶ ሀያ ሦስት። 22 የኔፆፋ ሰዎች፥ አምሳ ስድስት። 23 የዓናቶት ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት። 24 የዓዝማቬት ልጆች፥ አርባ ሁለት። 25 የቂርያትዓሪም፥ ከፊራና ብኤሮት ልጆች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት። 26 የራማና የጋባዕ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ። 27 የሚክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት። 28 የቤት-ኤልና የዐይ ሰዎች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት። 29 የንቦ ልጆች፥ አምሳ ሁለት። 30 የማግቢሽ ልጆች፥ አንድ መቶ አምሳ ስድስት። 31 የሌላኛው ዔላም ልጆች፥ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 32 የሐሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ። 33 የሎድ የሐዲድና የኦኖ ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አምስት። 34 የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት። 35 የስናአ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ። 36 ካህናቱ ከኢያሱ ቤት የሆነው ይዳዕያ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። 37 የኢሜር ልጆች፥ አንድ ሺህ አምሳ ሁለት። 38 የፓሽሑር ልጆች፥ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። 39 የሐሪም ልጆች፥ አንድ ሺህ ዐሥራ ሰባት። 40 ሌዋውያኑ፥ ከሆዳቭያ ወገን የኢያሱና የቃድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት። 41 መዘምራኑ፦ የአሳፍ ልጆች፥ አንድ መቶ ሀያ ስምንት። 42 የበር ጠባቂዎች ልጆች፦ የሻሉም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጣልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሾባይ ልጆች፥ ሁሉ አንድ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ። 43 የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ የፂሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ የጣባዖት ልጆች 44 የቄሮስ ልጆች፥ የሲዓሃ ልጆች፥ የፓዶን ልጆች፥ 45 የልባና ልጆች፥ የሐጋባ ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ 46 የሐጋብ ልጆች፥ የሻምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ 47 የጊድል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የርአያ ልጆች፥ 48 የረፂን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ የጋዛም ልጆች፥ 49 የዑዛ ልጆች፥ የፓሴሐ ልጆች፥ የቤሳይ ልጆች፥ 50 የአስና ልጆች፥ የምዒኒም ልጆች፥ የንፊሲም ልጆች፥ 51 የባቅቡቅ ልጆች፥ የሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥ 52 የባፅሉት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሻ ልጆች፥ 53 የባርቆስ ልጆች፥ የሲሥራ ልጆች፥ የታማሕ ልጆች፥ 54 የንፂሐ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች። 55 የሰሎሞንም አገልጋዮች ልጆች፦ የሶጣይ ልጆች፥ የሃሶፌሬት ልጆች፥ የፕሩዳ ልጆች፥ 56 የያዕላ ልጆች፥ የዳርቆን ልጆች፥ የጊዴል ልጆች፥ 57 የሽፋጥያ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፎኬሬት ሃፂባይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች። 58 እነዚህ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ሁሉና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። 59 ከቴልሜላሕ፥ ቴልሐርሻ፥ ክሩብ፥ ዓዳን፥ ኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስታወቅ አልቻሉም፤ 60 የድላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የንቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት ነበሩ። 61 ከካህናቱም ልጆች፦ የሖባያ ልጆች፥ የሃቆፅ ልጆች፥ የባርዚላይ ልጆች ከገለዓዳዊው ባርዚላይ ሚስት ያገባ፥ በስማቸውም የተጠራ ነው። 62 እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኙም፤ እንደ ርኩሳን ከክህነት ተከለከሉ። 63 አስተዳዳሪውም፦ በኡሪምና በቱሚም የሚጠይቅ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከቅዱሰ ቅዱሳን አትበሉም አላቸው። 64 ከምርኮ የተመለሱ ሰዎች አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ። 65 በተጨማሪም ወንዶች አገልጋይዮቻቸውና ሴቶች አገልጋዮቻቸው እነዚህ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ነበሩ ሌላ ሁለት መቶ ወንዶች መዘምራንና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው። 66 ፈረሶቻቸው ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎዎቻቸው ሁለት መቶ አርባ አምስት፥ 67 ግመሎቻቸው አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ። 68 ከአባቶች ቤቶች አለቆች አንዳንዶች፥ በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ጌታ ቤት በመጡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው እንዲሠራ በፈቃዳቸው መባ ሰጡ። 69 ስድሳ አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህ ምናን ብር፥ አንድ መቶ የካህናት ልብስ እንደየአቅማቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ። 70 ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንዶች፥ መዘምራኑ፥ በር ጠባቂዎቹና፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፥ በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ። |