Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐጌ 2:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ለይሁዳ አለቃ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፥ ለታላቁም ካህን ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ፥ ለቀሩትም ሕዝብ እንዲህ ስትል ተናገር፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ለይሁዳ ገዥ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፣ ለሊቀ ካህናቱ ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ፣ ከምርኮ ለተረፈውም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር፤ እንዲህም ብለህ ጠይቃቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ለይሁዳ ገዢ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፥ ለታላቁ ካህን ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ፥ ለቀሩትም ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ጌታ ይሁዳ ገዢ ለሆነው ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፥ ሊቀ ካህናት ለሆነው ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱና ተርፎ ከስደት ለተመለሰው ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ለይሁዳ አለቃ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፥ ለታላቁም ካህን ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ፥ ለቀሩትም ሕዝብ እንዲህ ስትል ተናገር፦

Ver Capítulo Copiar




ሐጌ 2:2
7 Referencias Cruzadas  

በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ አለቃ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤል፥ ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦


እግዚአብሔርም የይሁዳን አለቃ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፥ የታላቁንም ካህን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስ፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አስነሣ፣ በንጉሡም በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በሀያ አራተኛው ቀን መጡ፥ የአምላካቸውንም የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤት ሠሩ።


ሕቴ​ር​ሰታ ነህ​ም​ያም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝ​ቡ​ንም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሌዋ​ው​ያን ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ዛሬ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ አት​ዘኑ፤ አታ​ል​ቅ​ሱም” አሉ​አ​ቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕ​ጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለ​ቅሱ ነበ​ርና።


ሐቲ​ር​ሰ​ስ​ታም፥ “በኡ​ሪ​ምና በቱ​ሚም የሚ​ፈ​ርድ ካህን እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ከቅ​ዱሰ ቅዱ​ሳኑ አት​በ​ሉም” አላ​ቸው።


የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮ​ስም የመ​ዝ​ገብ ሐላፊ በነ​በ​ረው በሚ​ት​ሪ​ዳጡ እጅ አወ​ጣ​ቸው፤ ለይ​ሁ​ዳም መስ​ፍን ለሲ​ሳ​ብ​ሳር ቈጠ​ራ​ቸው።


የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ካህ​ናቱ፥ የሰ​ላ​ት​ያ​ልም ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም ተነ​ሥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ መሠ​ዊያ ሠሩ።


የሰላትያልም ልጅ ዘሩባቤል፥ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ድምፅ የነቢዩንም የሐጌን ቃል፥ አምላካቸው እግዚአብሔር እንደ ላከው ሁሉ ሰሙ፣ ሕዝቡም በእግዚአብሔር ፊት ፈሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios