Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -


ዕዝራ 2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


ከምርኮ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ሰዎች ዝርዝር
( ነህ. 7፥4-73 )

1 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ወደ ባቢሎን ከወሰዳቸው ሰዎች መካከል ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸውም የተመለሱት እነዚህ ናቸው።

2 ለተመለሱትም ስደተኞች መሪዎች ሆነው የመጡት ዘሩባቤል፥ ኢያሱ፥ ነህምያ፥ ሠራያ፥ ረዔላያ፥ መርዶክዮስ፥ ቢልሻን፥ ሚስፓር፥ ቢግዋይ፥ ሬሁምና በዓና ተብለው የሚጠሩት ነበሩ። ከእያንዳንዱ እስራኤላዊ ጐሣ በመሰባሰብ ወደ ሀገር የተመለሱትም ስደተኞች ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦

3-20 ከፓርዖሽ ወገን 2172 ከሸፋጥያ ወገን 372 ከአራሕ ወገን 775 ከፓሐትሞአብ ወገን የኢያሱና የኢዮአብ ዘሮች 2812 ከዔላም ወገን 1254 ከዛቱ ወገን 945 ከዛካይ ወገን 760 ከባኒ ወገን 642 ከቤባይ ወገን 623 ከዓዝጋድ ወገን 1222 ከአዶኒቃም ወገን 666 ከቢግዋይ ወገን 2056 ከዓዲን ወገን 454 በሕዝቅያስ በኩል ከአጤር ወገን 98 ከቤጻይ ወገን 323 ከዮራ ወገን 112 ከሐሹም ወገን 223 ከጊባር ወገን 95

21-35 ከምርኮ ከተመለሱትም ሰዎች መካከል በተለይ የቀድሞ አባቶቻቸው ከዚህ በሚከተሉት ከተሞች ይኖሩ የነበሩት ዝርዝር ይህ ነው፦ የቤተልሔም ተወላጆች 123 የነጦፋ ተወላጆች 56 የዐናቶት ተወላጆች 128 የዓዝማዌት ተወላጆች 42 የቂርያትይዓሪም፥ የከፊራና የበኤሮት ተወላጆች 743 የራማና የጌባዕ ተወላጆች 621 የሚክማስ ተወላጆች 122 የቤትኤልና የዐይ ተወላጆች 223 የነቦ ተወላጆች 52 የማግቢሽ ተወላጆች 156 የሌላይቱ ዔላም ተወላጆች 1254 የሓሪም ተወላጆች 320 የሎድ፥ የሐዲድና የኦኖ ተወላጆች 725 የኢያሪኮ ተወላጆች 345 የሰናአ ተወላጆች 3630

36-39 ከዚህ የሚከተለው ደግሞ ከምርኮ የተመለሱ የካህናት ቤተሰብ ዝርዝር ነው፦ የኢያሱ ዘር የሆነው የይዳዕያ ቤተሰብ 973 የኢሜር ቤተሰብ 1052 የፓሽሑር ቤተሰብ 1247 የሓሪም ቤተሰብ 1017

40-42 ከምርኮ የተመለሱት የሌዋውያን ቤተሰቦች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የሆዳውያ ዘሮች የሆኑት የኢያሱና የቃድሚኤል ቤተሰቦች 74 የአሳፍ ዘሮች የሆኑት የቤተ መቅደስ መዘምራን ብዛት 128 የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች የሆኑት የሻሉም፥ የአጤር፥ የጣልሞን፥ የዓቁብ፥ የሐጢጣና የሾባይ ዘሮች 139

43-54 ለቤተ መቅደስ ሥራ ከተመደቡትም መካከል ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥ ቄሮስ፥ ሲዓሃ፥ ፋዶን፥ ለባና፥ ሐጋባ፥ ዓቁብ፥ ሐጋብ፥ ሻምላይ፥ ሐናን፥ ጊዴል፥ ጋሐር፥ ረአያ፥ ረጺን፥ ነቆዳ፥ ጋዛም፥ ዑዛ፥ ፓሴሐ፥ ቤሳይ፥ አስና፥ መዑኒም፥ ነፊሲም፥ ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥ ባጽሉት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥ ባርቆስ፥ ሲሣራ ቴማሕ፥ ነጺሐና ሐጢፋ።

55-57 ከሰሎሞን አገልጋዮችም ወገን ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች፥ ሶጣይ፥ ሀሶፌሬት፥ ፐሩዳ፥ ያዕላ፥ ዳርቆን፥ ጊዴል፥ ሸፋጥያ፥ ሐጢል፥ ፖኬሬት፥ ሐጸባይምና አሚ ተብለው የሚጠሩ ናቸው።

58 ለቤተ መቅደስ ሥራ የተመደቡት ወገኖችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች ጠቅላላ ድምር 392 ነበር።

59-60 ቴልሜላሕ፥ ቴልሐርሻ፥ ከሩብ፥ አዳንና ኢሜር ተብለው ከሚጠሩት ከተሞች ከምርኮ የተመለሱ ነበሩ፤ ነገር ግን የእነርሱ ዘር ከእስራኤል ወገን መሆኑን ሊያስረዱ አልቻሉም። የደላያ፥ የጦቢያና የነቆዳ ጐሣዎች ወገኖችም 652 ነበሩ፤

61-62 ከዚህ የሚከተሉት የካህናት ጐሣዎች ሐባያ፥ ሀቆጽና ባርዚላይ የቀድሞ አባቶች እነማን እንደ ነበሩ ካለማወቃቸውም የተነሣ ካህናት ሆነው ለማገልገል ተቀባይነት አላገኙም። (ባርዚላይ ከገለዓዳዊው የባርዚላይ ልጆች አንድዋን አግብቶ በዚሁ ስም ይጠራ ነበር)።

63 በኡሪምና በቱሚም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ የሚችል ካህን እስከሚነሣም ድረስ እነርሱ የተቀደሰውን ምግብ መብላት እንደማይችሉ ገዢው አዘዛቸው።

64-67 በዚህም ሁኔታ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ጠቅላላ ብዛት 42360 ነበር። የእነርሱም ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ብዛት 7337 ሲሆን፥ የወንዶችና ሴቶች መዘምራን ድምር 200 ነበር። ምርኮኞቹም፦ 736 ፈረሶች፥ 245 በቅሎዎች፥ 435 ግመሎችና 6720 አህዮች ነበሩአቸው።

68 እነዚህም ምርኮኞች ተመልሰው በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወደነበረበት ስፍራ በደረሱ ጊዜ አንዳንድ የቤተሰብ መሪዎች ቀድሞ በነበረበት ቦታ ቤተ መቅደሱን እንደገና መልሶ ለመሥራት ይረዳ ዘንድ በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ የመባ ስጦታ አበረከቱ።

69 እነርሱም ለቤተ መቅደሱ ሥራ ማከናወኛ የሚችሉትን ያኽል አዋጥተው ያቀረቡት ስጦታ ሲደመር አምስት መቶ ኪሎ ወርቅ፥ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ስድስት ኪሎ ብር ሆነ፤ ለካህናቱም የሚሆን አንድ መቶ የካህናት ልብስ ሰጡ።

70 ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና ከሕዝቡም አንዳንዱ በኢየሩሳሌም ወይም በአቅራቢያዋ ሰፈሩ፤ መዘምራኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎችና ለቤተ መቅደሱ ሕንጻ የተመደቡት ሠራተኞች በየአቅራቢያው በሚገኙት ከተሞች ሰፈሩ፤ እንዲሁም የቀሩት እስራኤላውያን የቀድሞ አባቶቻቸው በነበሩባቸው ከተሞች ሰፈሩ።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos