ነህምያ 10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)በጽሑፉ ላይ ያተሙት ሰዎች 1 ያተሙትም እነዚህ ናቸው፤ የሐካልያ ልጅ ሐቴርሰታ ነህምያ፥ ሴዴቅያስ፤ 2 ኦርያ፥ ዓዛርያ፥ ኤርምያስ፤ 3 ፋሲኩር፥ አማርያ፥ ሚልክያ፤ 4 ሐጡስ፥ ሰባንያ፥ መሉክ፤ 5 ካሪም፥ ሚራሞት፥ አብድያ፤ 6 ዳንኤል፥ ገንቶን፥ ባሩክ፤ 7 ሜሱላም፥ አብድያ፥ ሚያሚን፤ 8 መዓዝያ፥ ቤልጋይ፥ ሰማያ፤ እነዚህ ካህናት ነበሩ። 9 ሌዋውያኑም የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ ከኢንሐዳድ ልጆች ባንዩ፥ ቀዳምኤል፤ 10 ወንድሞቹም ሰባንያ፥ ሆዲያ፥ ቆሊጣ፥ ፌልዕያ፥ ሐናን፤ 11 ሚካ፥ ሬሆብ፥ ሐሳብያ፤ 12 ዘኩር፥ ሰራብያ፥ ሰባንያ፤ 13 ሆድያ፥ ባኒ፥ ባኑን። 14 የሕዝቡ አለቆች ፋሮስ፥ ፈሐት ሞዓብ፥ ኤላም፥ ዛቱያ፥ ባኒ፤ 15 ቡኒ፥ ዓዝጋድ፥ ቤባይ፤ 16 አዶንያስ፥ በጉዋይ፥ ዓዲን፤ 17 አጤር፥ ሕዝቅያስ፥ ዓዙር፤ 18 አሆዲያ፥ ሐሱም፥ ቤሳይ፤ 19 ሐሪፍ፥ ዓናቶት፥ ኖባይ፤ 20 መግፈአስ፥ ሜሱላም፥ ኤዚር፤ 21 ሜሴዜቤል፥ ሳዶቅ፥ ያዱአ፤ 22 ፈላጥያ፥ ሐናን፥ ዓናያ፤ 23 ሆሴዕ፥ ሐናንያ፥ አሱብ፥ 24 አሎኤስ፥ ፈሊሃ፥ ሶቤቅ፤ 25 ሬሁም፥ ሐሰብና፥ መዕሤያ፤ 26 አሂያ፥ ሐናን፥ ዓናን፥፤ 27 መሎክ፥ ሔራም፥ ባዕና። ሕዝቡ የገቡት ቃል ኪዳን 28 የቀሩትም ሕዝብ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በረኞቹም፥ መዘምራንም፥ ናታኒምም፥ ከምድርም አሕዛብ ራሳቸውን የለዩና ወደ እግዚአብሔር ሕግ የገቡ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉትም ሁሉ ወንድሞቻቸውንና ታላላቆቻቸውን አበረታቱ፤ 29 በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ፥ ፍርዱንም፥ ሥርዐቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ርግማንንና መሐላን አደረጉ። 30 ሴቶች ልጆቻችንንም ለምድር አሕዛብ አንሰጥም፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችን አንወስድም፤ 31 የምድርንም አሕዛብ ሸቀጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገበዩ በሰንበት ቀን ቢያመጡ በሰንበት ወይም በተቀደሰው ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ ሰባተኛውንም ዓመት እናከብራለን፤ ከሰውም ዕዳ ማስከፈልን እንተዋለን። 32 ስለ አምላካችንም ቤት ሥራ ሁሉ በየዓመቱ የሰቅል ሢሶ እናመጣ ዘንድ ሥርዐት በራሳችን ላይ እናደርጋለን። 33 ስለ አምላካችንም ቤት አገልግሎት፥ ስለ ኅብስተ ገጽም፥ ዘወትርም በሰንበትና በመባቻ ስለ ማቅረብ ስለ እህሉ ቍርባንና ስለሚቃጠለው መሥዋዕት፥ ስለ በዓላትም፥ ስለ ተቀደሱትም ነገሮች፥ ለእስራኤልም ስለሚያስተሰርየው ስለ ኀጢአት መሥዋዕት፥ 34 እኛም ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ ዕንጨት ቍርባን ዕጣ ተጣጣልን፤ 35 በየዓመቱም የመሬታችንን እህል ቀዳምያት፥ የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ቀዳምያት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥ 36 በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥ 37 የእህላችንንም ቀዳምያት፥ የዛፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወይኑንና የዘይቱንም ፍሬ ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ ዐሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን ዐሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን። 38 ሌዋውያኑም ዐሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፤ ሌዋውያኑም የዐሥራቱን ዐሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት። 39 የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንም ቀዳምያት፥ የመቅደሱን ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት፥ በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፤ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም። |