Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 10:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 የእ​ህ​ላ​ች​ን​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የዛ​ፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወ​ይ​ኑ​ንና የዘ​ይ​ቱ​ንም ፍሬ ወደ ካህ​ናቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ጓዳ​ዎች እና​መጣ ዘንድ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን እርሻ ሁሉ ዐሥ​ራት ይቀ​በ​ላ​ሉና የመ​ሬ​ታ​ች​ንን ዐሥ​ራት ወደ ሌዋ​ው​ያን እና​መጣ ዘንድ ማልን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 “ከዚህም በላይ የቡሖአችንን፣ የእህል ቍርባናችንን፣ የዛፎቻችንን ፍሬ ሁሉ፣ አዲሱን የወይን ጠጃችንንና የዘይታችንን በኵራት ወደ ካህናቱ፣ ወደ አምላካችን ቤት ዕቃ ቤቶች እናመጣለን። እኛ በምንሠራባቸው ከተሞች ሁሉ ያለውን ዐሥራት የሚሰበስቡት ሌዋውያን ስለ ሆኑ፣ የሰብላችንን ዐሥራት ወደ ሌዋውያኑ እናመጣለን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 የእህላችንንም በኵራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቁርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ከሰበሰብነው መከር የመጀመሪያውን እህል ዱቄት ወስደን በቤተ መቅደስ ለሚያገለግለው ካህን እንሰጣለን፤ ሌላውንም የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይትና የመሳሰለውንም ፍራ ፍሬ ሁሉ የመጀመሪያውን መባ አድርገን እናቀርባለን። ከእርሻ መንደሮቻችን ግብር ለሚሰበስቡት ሌዋውያንም ምድራችን ከምታበቅለው የእህል መከር ዐሥራት እያወጣን እንሰጣለን።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 10:37
23 Referencias Cruzadas  

ከየ​ማ​ደ​ሪ​ያ​ችሁ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት የተ​ሠራ ሁለት የቍ​ር​ባን እን​ጀራ ታመ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ህ​ላ​ችሁ ቀዳ​ም​ያት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሾ ይጋ​ገ​ራል።


“ለሌ​ዊም ልጆች እነሆ፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ስለ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዐሥ​ራት ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ዕቃ ቤቶ​ቹ​ንም እን​ዲ​ያ​ነጹ አዘ​ዝሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ​ዎች፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ ዕጣ​ኑ​ንም መልሼ በዚያ አገ​ባሁ።


ለሌ​ዋ​ው​ያን፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ንና ለበ​ረ​ኞቹ እንደ ሕጉ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ህ​ሉን ቍር​ባ​ንና ዕጣ​ኑን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም፥ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት፥ ለካ​ህ​ና​ቱም የሆ​ነ​ውን ቀዳ​ም​ያ​ቱን አስ​ቀ​ድሞ ያስ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትን ታላቅ ዕቃ ቤት አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ለት ነበር።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከም​ት​ሰ​በ​ስ​በው ፍሬ ሁሉ ቀዳ​ም​ያት ውሰድ፤ በዕ​ን​ቅ​ብም አድ​ር​ገው፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።


የእ​ህ​ል​ህን፥ የወ​ይ​ን​ህን፥ የዘ​ይ​ት​ህ​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ አስ​ቀ​ድ​ሞም የተ​ሸ​ለ​ተ​ውን የበ​ግ​ህን ጠጕር ለእ​ርሱ ትሰ​ጣ​ለህ።


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።


በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች የሚ​ኖሩ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የይ​ሁዳ ልጆች የበ​ሬ​ዉ​ንና የበ​ጉን፥ የፍ​የ​ሉ​ንም ዐሥ​ራት አመጡ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀደ​ሱት፤ ከም​ረ​ውም አኖ​ሩት።


እር​ሾው ቅዱስ ከሆነ ቡሆ​ውም እን​ዲሁ ቅዱስ ነው፤ ሥርዋ ቅዱስ ከሆ​ነም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ እን​ዲሁ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናሉ።


“ከእ​ር​ሻህ ዘር​ተህ በየ​ዓ​መቱ ከም​ታ​ገ​ኘው እህ​ልህ ሁሉ ዐሥ​ራት ታወ​ጣ​ለህ።


ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ፈን​ታ​ቸው እን​ዳ​ል​ተ​ሰጠ፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም ሌዋ​ው​ያ​ንና መዘ​ም​ራን እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ እር​ሻው እንደ ሄደ ተመ​ለ​ከ​ትሁ።


ይሁ​ዳም ሁሉ የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን የዘ​ይ​ቱ​ንም ዐሥ​ራት ወደ ዕቃ ቤቶች አመጡ።


“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”


ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ ለይ፤ ከመ​ን​ጋ​ህና ከከ​ብ​ት​ህም መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለ​ደው ተባት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሆ​ናል።


ከሰው እስከ እን​ስሳ ቢሆን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለድ ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ነገር ግን የሰ​ውን በኵ​ራት ፈጽሞ ትቤ​ዠ​ዋ​ለህ፤ ያል​ነ​ጹ​ት​ንም እን​ስ​ሳት በኵ​ራት ትቤ​ዣ​ለህ።


ሥጋ​ውም ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ፍር​ምባ እንደ ቀኙም ወርች ለአ​ንተ ይሆ​ናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios