Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮ​ስም የመ​ዝ​ገብ ሐላፊ በነ​በ​ረው በሚ​ት​ሪ​ዳጡ እጅ አወ​ጣ​ቸው፤ ለይ​ሁ​ዳም መስ​ፍን ለሲ​ሳ​ብ​ሳር ቈጠ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በግምጃ ቤቱ ኀላፊ በሚትሪዳጡ አማካይነት ንዋያተ ቅድሳቱ እንዲመጡና በይሁዳው ገዥ በሰሳብሳር ፊት እንዲቈጠሩ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የፋርስ ንጉሥ ቂሮስም በመዝገብ ቤቱ በሚትረዳት እጅ አወጣቸው፥ ለይሁዳም መስፍን ለሼሽባጻር ቆጠራቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የፋርሱ ንጉሥ ቂሮስ እነዚያን ንዋያተ ቅድሳት ሚትረዳት ተብሎ በሚጠራው በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ኀላፊ አስቈጥሮ የይሁዳ ገዢ ለሆነው ለሼሽባጻር አስረከበው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የፋርስ ንጉሥ ቂሮስም በመዝገቡ ላይ በነበረው በሚትሪዳጡ እጅ አወጣቸው፤ ለይሁዳም መስፍን ለሰሳብሳር ቈጠራቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 1:8
10 Referencias Cruzadas  

የወ​ር​ቁና የብሩ ዕቃ​ዎች ሁሉ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሁሉ ሲሳ​ብ​ሳር ከባ​ቢ​ሎን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ከተ​መ​ለሱ ምር​ኮ​ኞች ጋር ወሰደ።


ከዘ​ሩ​ባ​ቤል፥ ከኢ​ያሱ፥ ከነ​ህ​ምያ፥ ከሠ​ራያ፥ ከሮ​ሃ​ልያ፥ ከመ​ር​ዶ​ክ​ዮስ፥ ከበ​ላ​ሳን፥ ከመ​ሴ​ፋር፥ ከበ​ጎ​ዋይ፥ ከሬ​ሁም፥ ከበ​ዓና ጋር መጡ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤


ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ረው መቅ​ደስ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወደ ባቢ​ሎ​ንም መቅ​ደስ ያፈ​ለ​ሰ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የወ​ር​ቁ​ንና የብ​ሩን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባ​ቢ​ሎን መቅ​ደስ አው​ጥቶ ለቤተ መዛ​ግ​ብቱ ሹም ለሲ​ሳ​ብ​ሳር ሰጠ​ውና፦


በዚያ ጊዜም ይህ ሲሳ​ብ​ሳር መጣ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሠ​ረተ፤ ከዚ​ያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየ​ተ​ሠራ አል​ተ​ጨ​ረ​ሰም።


በዚ​ያን ጊዜም የሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ ተነ​ሥ​ተው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመሩ፤ የሚ​ያ​ግ​ዙ​አ​ቸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።


በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ የዋ​ጠ​ች​ው​ንም ከአ​ፍዋ አስ​ተ​ፋ​ታ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብም ከዚያ ወዲያ ወደ እር​ስዋ አይ​ሰ​በ​ሰ​ቡም፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ቅጥ​ሮች ይወ​ድ​ቃሉ።


በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ አለቃ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤል፥ ወደ ታላቁም ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦


እግዚአብሔርም የይሁዳን አለቃ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፥ የታላቁንም ካህን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስ፥ የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አስነሣ፣ በንጉሡም በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በሀያ አራተኛው ቀን መጡ፥ የአምላካቸውንም የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤት ሠሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos