በታቦቷም ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው የቃል ኪዳን ጽላት ከሚባሉት ከሁለቱ የድንጋይ ጽላት በቀር ምንም አልነበረባትም።
ዘፀአት 25:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በታቦቱም ውስጥ እኔ የምሰጥህን ምስክር ታስቀምጣለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምሰጥህንም ምስክር በታቦቱ ውስጥ አኑር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ አኑር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ እኔ የምሰጥህን፥ ትእዛዞቹ የተጻፉባቸውን ሁለት ጽላቶች በታቦቱ ውስጥ አኑር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታቦቱም ውስጥ እኔ የምሰጥህን ምስክር ታስቀምጣለህ። |
በታቦቷም ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው የቃል ኪዳን ጽላት ከሚባሉት ከሁለቱ የድንጋይ ጽላት በቀር ምንም አልነበረባትም።
የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ አነገሡትም፤ ኢዮአዳና ልጆቹም አነገሡት፥ “ንጉሡ በሕይወት ይኑር” እያሉም ቀቡት።
መጋረጃውንም በምሰሶዎች ላይ ስቀለው፤ በመጋረጃውም ውስጥ የምስክሩን ታቦት አግባው፤ መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ።
በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋረጃ ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ያብሩት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃቸው የዘለዓለም ሥርዐት ይሁን።
ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፤ ታልመውማለህ፤ ከዚያም ለአንተ በምገለጥበት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። እርሱም ቅዱሰ ቅዱሳን ይሁንላችሁ።
እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ ሁለቱን የምስክር ጽላት፥ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።
ሙሴም ተመለሰ፤ ሁለቱንም የምስክር ጽላት በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ፤ የድንጋይ ጽላቱም በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር።
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ሁለቱ ጽላት በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር ፊቱ እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር።
በካህኑ በአሮን ልጅ በይታምር እጅ የሌዋውያን ተልእኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእግዚአብሔር እንደታዘዘ የምስክሩ ድንኳን ሥርዐት ይህ ነው።
ሙሴም ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፤ መሎጊያዎቹንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አደረገ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው።
“ይህን የሕግ መጽሐፍ ውሰዱ፤ በዚያም በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት።
በውስጥዋም የወርቅ ማዕጠንትና ሁለንተናዋን በወርቅ የለበጡአት፥ የኪዳን ታቦት፥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የለመለመችው የአሮን በትር፥ የኪዳኑም ጽላት ነበሩባት።