Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በው​ስ​ጥ​ዋም የወ​ርቅ ማዕ​ጠ​ን​ትና ሁለ​ን​ተ​ና​ዋን በወ​ርቅ የለ​በ​ጡ​አት፥ የኪ​ዳን ታቦት፥ መና ያለ​ባት የወ​ርቅ መሶ​ብና የለ​መ​ለ​መ​ችው የአ​ሮን በትር፥ የኪ​ዳ​ኑም ጽላት ነበ​ሩ​ባት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንትና በወርቅ የተለበጠው የኪዳኑ ታቦት ነበሩ፤ ይህም ታቦት መና ያለበትን የወርቅ መሶብ፣ የለመለመችውን የአሮንን በትርና ኪዳኑ የተጻፈበትን ጽላት ይዟል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበር፤ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፥ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በዚህችኛዋ ክፍል ውስጥ የወርቅ ማዕጠንትና በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት ነበሩባት፤ ከዚህችም የኪዳን ታቦት ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብ፥ ለምልማ የነበረችው የአሮን በትር፥ ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባት ጽላት ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበረ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፤ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ፥

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 9:4
26 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ማጕ​ረ​ም​ረ​ማ​ቸው ከእኔ ዘንድ እን​ዲ​ጠፋ፥ እነ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ሞቱ ለማ​ይ​ሰሙ ልጆች ምል​ክት ሆና ትጠ​በቅ ዘንድ የአ​ሮ​ንን በትር በም​ስ​ክሩ ፊት አኑር።”


በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው ከሁ​ለቱ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከአ​ለው መሠ​ዊያ ላይ የእ​ሳት ፍም አም​ጥቶ ጥና​ውን ይሞ​ላል፤ ከተ​ወ​ቀ​ጠ​ውም ልቅ​ምና ደቃቅ ዕጣን እጁን ሙሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ወደ መጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ ያመ​ጣ​ዋል።


በእ​ር​ሱም ውስጥ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት ታኖ​ራ​ለህ፤ ታቦ​ቱ​ንም በመ​ጋ​ረጃ ትጋ​ር​ዳ​ለህ።


መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም በም​ሰ​ሶ​ዎች ላይ ስቀ​ለው፤ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት አግ​ባው፤ መጋ​ረ​ጃ​ውም በቅ​ድ​ስ​ቱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ መካ​ከል መለያ ይሁ​ና​ችሁ።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የመ​ረ​ጥ​ሁት ሰው በትር ትለ​መ​ል​ማ​ለች፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ባ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማጕ​ረ​ም​ረም ከእኔ ዘንድ አጠ​ፋ​ለሁ።”


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወ​ረደ ጊዜ ሁለቱ ጽላት በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተ​ራ​ራው በወ​ረደ ጊዜ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ሲነ​ጋ​ገር ፊቱ እን​ዳ​ን​ጸ​ባ​ረቀ አላ​ወ​ቀም ነበር።


ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።


ከግ​ብ​ፅም ምድር ባወ​ጣ​ቸው ጊዜ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ያደ​ረ​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ላለ​ባት ታቦት ስፍ​ራን በዚያ አደ​ር​ግ​ሁ​ላት።


በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው የቃል ኪዳን ጽላት ከሚ​ባ​ሉት ከሁ​ለቱ የድ​ን​ጋይ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም።


ከጥሩ ወር​ቅም የተ​ሠ​ሩ​ትን ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽን​ሐ​ሖ​ችን፥ ለው​ስ​ጠ​ኛ​ውም ቤት ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅ​ደ​ሱም ደጆች የሚ​ሆ​ኑ​ትን የወ​ርቅ ማጠ​ፊ​ያ​ዎች አሠራ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በነ​ጋው ሙሴና አሮን ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆ​ነች የአ​ሮን በትር አቈ​ጠ​ቈ​ጠች፤ ለመ​ለ​መ​ችም፤ አበ​ባም አወ​ጣች፤ የበ​ሰለ ለው​ዝም አፈ​ራች።


የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ታቦት፥ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።


ሙሴም ተመ​ለሰ፤ ሁለ​ቱ​ንም የም​ስ​ክር ጽላት በእጁ ይዞ ከተ​ራ​ራው ወረደ፤ የድ​ን​ጋይ ጽላ​ቱም በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለት ወገን ተጽ​ፎ​ባ​ቸው ነበር።


የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ፤ ርዝ​መቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱ አንድ ክንድ፤ አራት ማዕ​ዘን ነበር፤ ከፍ​ታ​ውም ሁለት ክንድ ነበር፤ ቀን​ዶ​ቹም ከእ​ርሱ ጋር በአ​ን​ድ​ነት የተ​ሠሩ ነበሩ።


ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ባ​ቸ​ውን የቃል ኪዳን ጽላት እቀ​በል ዘንድ ወደ ተራራ በወ​ጣሁ ጊዜ፥ በተ​ራ​ራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀ​ምጬ ነበር፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም።


ከአ​ርባ ቀንና ከአ​ርባ ሌሊ​ትም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ የቃል ኪዳ​ኑን ጽላት ሰጠኝ።


በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios