2 ዜና መዋዕል 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ አነገሡትም፤ ኢዮአዳና ልጆቹም አነገሡት፥ “ንጉሡ በሕይወት ይኑር” እያሉም ቀቡት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ዮዳሄና ወንዶች ልጆቹ የንጉሡን ልጅ አምጥተው ዘውድ ጫኑለት፤ ኪዳኑንም ሰጥተው አነገሡት፤ ቀብተውም፣ “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” እያሉ ጮኹ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 የንጉሡንም ልጅ አውጥተው ዘውዱን ጫኑበት፥ ምስክሩንም ሰጡት፥ አነገሡትም፤ ዮዳሄና ልጆቹም፦ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ ቀቡት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ከዚህ በኋላ ዮዳሄ ኢዮአስን አውጥቶ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነበት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጅ አስረከበው፤ በዚህ ዐይነት ካህኑ ዮዳሄና ልጆቹ ኢዮአስን ቀብተው አነገሡት፤ ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ!” በማለት ደስታቸውን ገለጡ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 የንጉሡንም ልጅ አውጥተው ዘውዱን ጫኑበት፤ ምስክሩንም ሰጡት፤ አነገሡትም፤ ዮዳሄና ልጆቹም “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ!” እያሉ ቀቡት። Ver Capítulo |