Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 23:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህ በኋላ ዮዳሄ ኢዮአስን አውጥቶ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነበት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጅ አስረከበው፤ በዚህ ዐይነት ካህኑ ዮዳሄና ልጆቹ ኢዮአስን ቀብተው አነገሡት፤ ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ!” በማለት ደስታቸውን ገለጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ዮዳሄና ወንዶች ልጆቹ የንጉሡን ልጅ አምጥተው ዘውድ ጫኑለት፤ ኪዳኑንም ሰጥተው አነገሡት፤ ቀብተውም፣ “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” እያሉ ጮኹ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የንጉሡንም ልጅ አውጥተው ዘውዱን ጫኑበት፥ ምስክሩንም ሰጡት፥ አነገሡትም፤ ዮዳሄና ልጆቹም፦ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ ቀቡት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አው​ጥቶ ዘው​ዱን ጫነ​በት፤ ምስ​ክ​ሩ​ንም ሰጠው፤ አነ​ገ​ሡ​ትም፤ ኢዮ​አ​ዳና ልጆ​ቹም አነ​ገ​ሡት፥ “ንጉሡ በሕ​ይ​ወት ይኑር” እያ​ሉም ቀቡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የንጉሡንም ልጅ አውጥተው ዘውዱን ጫኑበት፤ ምስክሩንም ሰጡት፤ አነገሡትም፤ ዮዳሄና ልጆቹም “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ!” እያሉ ቀቡት።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 23:11
34 Referencias Cruzadas  

በሚወድቅበት ጊዜ እንደሚሞት ዐውቅ ስለ ነበር ወደ እርሱ ቀርቤ ገደልኩት፤ ከዚህ በኋላ ዘውዱን ከራሱ ላይ፥ አንባሩንም ከክንዱ ላይ ወሰድኩ፤ ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ እነርሱን ለአንተ አመጣሁልህ።”


የዳዊት ታማኝ ወዳጅ ሑሻይ አቤሴሎምን ባገኘው ጊዜ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ይሁን!” እያለ ጮኸ።


እንግዲህ የእስራኤል መሪዎች ሁሉ በኬብሮን ወደ ነበረው ወደ ዳዊት የመጡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እርሱም ከእነርሱ ጋር በእግዚአብሔር ፊት የቃል ኪዳን ስምምነት አደረገ፤ እነርሱም ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።


አዶንያስ በዛሬው ዕለት ብዙ ጥጆችንና የሰቡ ኰርማዎችን፥ በጎችን ዐርዶ መሥዋዕት አቅርቦአል፤ ሌሎቹን የንጉሡን ልጆች የሠራዊትህን አዛዥ ኢዮአብንና ካህኑን አብያታርን ጋብዞአል፤ እነሆ አሁን በዚህ ሰዓት “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ አዶንያስ!” በማለት እየደነፉ ከእርሱ ጋር በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው።


በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን ቀብተው በእስራኤል ላይ ያንግሡት፤ ከዚህ በኋላ እምቢልታ በመንፋት ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ‘ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ ሰሎሞን!’ በሉ።


ካህኑ ሳዶቅም ከተቀደሰው ድንኳን ይዞት የመጣውን የቅባት ዘይት መያዣ ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው፤ በዚህን ጊዜ እምቢልታ ነፉ፤ ሕዝቡም ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ ሰሎሞን!” አሉ፤


ከዚያም በኋላ ዮዳሄ ኢዮአስን አውጥቶ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነበት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጂ አስረከበው፤ በዚህ ዐይነት ኢዮአስ ተቀብቶ ነገሠ፤ ሕዝቡም እያጨበጨበ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ!” አለ።


አካዝያስ፥ ይሆያዳዕ ተብሎ የሚጠራውን ካህን ያገባች ይሆሼባዕ ተብላ የምትጠራ እኅት ነበረችው፤ እርስዋም ከአካዝያስ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነውን ኢዮአስን ሊገድሉ ጥቂት ቀርቶአቸው ከነበሩት መሳፍንት መካከል በስውር ወስዳ እርሱንና ሞግዚቱን በቤተ መቅደስ አጠገብ በሚገኝ መኝታ ቤት ውስጥ ደበቀቻቸው፤ በዚህም ዐይነት በመደበቅ ኢዮአስን በዐታልያ እጅ ከመገደል አዳነችው፤


ሰይፋቸውን በእጃቸው ያያዙትን ጭፍሮች ሁሉ ንጉሡን ከአደጋ ለመከላከል በመሠዊያው በኩል በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ዙሪያውን ተሰልፈው እንዲቆሙ አደረጋቸው።


ዐታልያ ሕዝቡ ለንጉሡ ያደረገውን እልልታና ሆታ ሰምታ ሕዝብ ወደ ተሰበሰበበት ወደ ቤተ መቅደስ በፍጥነት መጣች።


ጠላቶቹ ኀፍረትን እንዲከናነቡ አደርጋቸዋለሁ፤ እርሱ ግን የሚያንጸባርቅ ዘውድ ይቀዳጃል።


በብዙ በረከትን ሰጥተህ ተቀበልከው፤ በራሱ ላይ የንጹሕ ወርቅ ዘውድ ደፋህለት።


እርሱ ሥርዓትን ለያዕቆብ ልጆች ዐወጀ፤ ለእስራኤልም ሕግን መሠረተ፤ ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ የቀድሞ አባቶቻችንን አዘዛቸው።


አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤ የተቀደሰ ዘይት ቀብቼም አነገሥኩት።


ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አፍርሰሃል፤ ዘውዱንም በዐፈር ላይ ጥለኸዋል።


ከዚህም በኋላ እኔ የምሰጥህን፥ ትእዛዞቹ የተጻፉባቸውን ሁለት ጽላቶች በታቦቱ ውስጥ አኑር።


በታቦቱ ላይ መክደኛውን አድርግ፤ የምሰጥህንም ጽላት በታቦቱ ውስጥ አኑረው፤


እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።


ነገሥታት አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል። የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቂአለሽ፤ የእኔን ርዳታ ለማግኘት የሚጠባበቁ ከቶ አያፍሩም።”


ምስክርነቱን ጠብቀህ ያዝ፤ በደቀ መዛሙርቴ ልብ ውስጥም ሕጉን አትም።


ይህን ቃል ባይናገሩ በእርግጥ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም።


ከሕዝቡም ፊት ለፊት ይሄዱ የነበሩትና ከኋላ ይከተሉ የነበሩት፥ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ምስጋና ይሁን! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና! ምስጋና በአርያም ለእግዚአብሔር ይሁን!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


አሁን ግን ከመላእክት ጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ የጫነውን ኢየሱስን እናያለን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞቶአል።


ጌታ በቃል ኪዳኑ መሠረት ለወዳጆቹ የሚሰጠውን የሕይወት አክሊል ስለሚቀበል ፈተናን ታግሦ የሚጸና ሰው የተባረከ ነው።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


ዐይኖቹ የእሳት ነበልባል ይመስላሉ፤ በራሱም ላይ ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱ በቀር ሌላ ማንም የማያውቀው በእርሱ ላይ የተጻፈ ስም ነበረ፤


ኻያ አራቱ ሽማግሌዎች ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚኖረው፥ በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዳሉ፤ አክሊሎቻቸውንም በዙፋኑ ፊት አኑረው፥ እንዲህ ይላሉ፦


እንዲሁም፥ በዙፋኑ ዙሪያ ኻያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ ኻያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።


ለአምላካችንም የካህናት መንግሥት እንዲሆኑ አድርገሃቸዋል፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ።”


ሳሙኤል የወይራ ዘይት መያዣውን ቀንድ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። ከዚያም በኋላ “እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ቀባህ፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ነግሠህ በዙሪያቸው ካሉ ጠላቶች ታድናቸዋለህ እግዚአብሔር በርስቱ ላይ የሾመህ ለመሆኑ ይህ ማስረጃ ነው፤


ሳሙኤልም ሕዝቡን “እግዚአብሔር የመረጠው ሰው እነሆ ይህ ነው! ከእኛም መካከል እርሱን የሚስተካከለው የለም” አለ። ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ ይሁን!” አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios