Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 40:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሙሴም ጽላ​ቱን ወስዶ በታ​ቦቱ ውስጥ አኖ​ረው፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም በታ​ቦቱ ቀለ​በ​ቶች ውስጥ አደ​ረገ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ አኖ​ረው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ምስክሩን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጠው፤ መሎጊያዎቹንም ከታቦቱ ጋራ አያያዛቸው፤ የስርየት መክደኛውንም በላዩ ላይ አደረገው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፥ መሎጊያዎቹንም በታቦቱ አደረገ፥ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች ወስዶ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ አስቀመጣቸው፤ መሎጊያዎችንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አስገባ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፥ መሎጊያዎቹን በታቦቱ ዘንድ አደረገ፥ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 40:20
19 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ ይጠ​በቅ ዘንድ አሮን በም​ስ​ክሩ ፊት አኖ​ረው።


እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።


በው​ስ​ጥ​ዋም የወ​ርቅ ማዕ​ጠ​ን​ትና ሁለ​ን​ተ​ና​ዋን በወ​ርቅ የለ​በ​ጡ​አት፥ የኪ​ዳን ታቦት፥ መና ያለ​ባት የወ​ርቅ መሶ​ብና የለ​መ​ለ​መ​ችው የአ​ሮን በትር፥ የኪ​ዳ​ኑም ጽላት ነበ​ሩ​ባት።


እን​ግ​ዲህ ምሕ​ረ​ትን እን​ድ​ን​ቀ​በል፥ በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንም ጊዜ የሚ​ረ​ዳ​ንን ጸጋ እን​ድ​ና​ገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእ​ም​ነት እን​ቅ​ረብ።


የኦ​ሪት ጽድቅ ፍጻ​ሜስ ለሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ ማመን ነው።


እር​ሱ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት የሚ​ገኝ፥ በደ​ሙም የሆነ ማስ​ተ​ስ​ረያ አድ​ርጎ አቆ​መው፤ ይህም ከጥ​ንት ጀምሮ በበ​ደ​ሉት ላይ ጽድ​ቁን ይገ​ልጥ ዘንድ ነው።


ኢየሱስም መልሶ “አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።


የበ​ደ​ልን ነገር በእኔ አወጡ። የተኛ ሰው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ነ​ቃ​ምን?


በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው የቃል ኪዳን ጽላት ከሚ​ባ​ሉት ከሁ​ለቱ የድ​ን​ጋይ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም።


ተመ​ል​ሼም ከተ​ራ​ራው ወረ​ድሁ፤ ጽላ​ቱ​ንም በሠ​ራ​ሁት ታቦት ውስጥ አደ​ረ​ግ​ኋ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘኝ በዚያ ኖሩ።


በእ​ር​ሱም ውስጥ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት ታኖ​ራ​ለህ፤ ታቦ​ቱ​ንም በመ​ጋ​ረጃ ትጋ​ር​ዳ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።


መጋ​ረ​ጃ​ውም የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ውስጥ ይጋ​ርድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው መጋ​ረ​ጃ​ውን በድ​ን​ኳኑ ላይ ዘረ​ጋው፤ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም መደ​ረ​ቢያ በላዩ አደ​ረ​ገ​በት።


ዳዊ​ትም ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ላት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው ከሁ​ለቱ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios