Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘፀአት 16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


መናና ድር​ጭት እንደ ወረ​ደ​ላ​ቸው

1 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ከኤ​ሎም ተጓዙ፤ ከግ​ብፅ ሀገር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በኤ​ሎ​ምና በሲና መካ​ከል ወዳ​ለ​ችው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።

2 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።

3 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አሉ​አ​ቸው፥ “በሥ​ጋው ምን​ቸት አጠ​ገብ ተቀ​ም​ጠን እስ​ክ​ን​ጠ​ግብ ድረስ እን​ጀ​ራና ሥጋ በም​ን​በ​ላ​በት ጊዜ በግ​ብፅ ምድር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ምነው በሞ​ትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልት​ገ​ድሉ እኛን ወደ​ዚች ምድረ በዳ አም​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና።”

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በሕጌ ይሄዱ ወይም አይ​ሄዱ እንደ ሆነ እኔ እን​ድ​ፈ​ት​ና​ቸው፥ እነሆ፥ ከሰ​ማይ እን​ጀ​ራን አዘ​ን​ብ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡም ወጥ​ተው ለዕ​ለት ለዕ​ለት የሚ​በ​ቃ​ቸ​ውን ይሰ​ብ​ስቡ።

5 እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ያመ​ጡ​ትን ያዘ​ጋጁ፤ ዕለት ዕለ​ትም ከሚ​ለ​ቅ​ሙት ይልቅ ሁለት እጥፍ ይሁን” አለው።

6 ሙሴና አሮ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ምድር እንደ አወ​ጣ​ችሁ ማታ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤

7 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ጥዋት ታያ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​ትን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ በእ​ኛም ላይ የም​ታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ እኛ ምን​ድን ነን?” አሉ።

8 ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​በ​ትን ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና በመሸ ጊዜ ትበሉ ዘንድ ሥጋን፥ በማ​ለ​ዳም ትጠ​ግቡ ዘንድ እን​ጀ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እኛም ምን​ድን ነን? ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይ​ደ​ለም” አለ።

9 ሙሴም አሮ​ንን፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ፦ ‘ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅረቡ’ በል” አለው።

10 አሮ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በተ​ና​ገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታ​ቸ​ውን አቀኑ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በደ​መ​ናው ታየ።

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፦

12 “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማን​ጐ​ራ​ጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ማለ​ዳም እን​ጀ​ራን ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”

13 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በመሸ ጊዜ ድር​ጭ​ቶች መጡ፤ ሰፈ​ሩ​ንም ሸፈ​ኑት፤ በማ​ለ​ዳም በሰ​ፈሩ ዙሪያ ጠል ወድቆ ነበር።

14 የወ​ደ​ቀው ጠል በአ​ለፈ ጊዜ፥ እነሆ፥ በመ​ሬት ላይ እንደ ውርጭ ነጭ ሆኖ ድን​ብ​ላል የሚ​መ​ስል ደቃቅ ነገር በም​ድረ በዳ ታየ።

15 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ዩት ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ምን​ድን ነው?” ተባ​ባሉ። ያ ምን እን​ደ​ሆነ አላ​ወ​ቁ​ምና። ሙሴም አላ​ቸው፥ “ትበሉ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጣ​ችሁ እን​ጀራ ይህ ነው።

16 ታደ​ር​ጉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፦ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ለቤተ ሰቡ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አንድ ጎሞር ይሰ​ብ​ስብ፤ እንደ ቤተ ሰቡ ቍጥር ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ በድ​ን​ኳኑ አብ​ረ​ውት ከሚ​ኖ​ሩት ጋር ይሰ​ብ​ስብ።”

17 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ አንዱ አብ​ዝቶ፥ አን​ዱም አሳ​ንሶ ሰበ​ሰበ።

18 በጎ​ሞ​ርም በሰ​ፈ​ሩት ጊዜ እጅግ ለሰ​በ​ሰበ አል​ተ​ረ​ፈ​ውም፤ ጥቂ​ትም ለሰ​በ​ሰበ አል​ጐ​ደ​ለ​በ​ትም፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ለየ​ቤቱ ሰበ​ሰበ።

19 ሙሴም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማንም ከእ​ርሱ አን​ዳች ለነገ አያ​ስ​ቀር” አላ​ቸው።

20 ነገር ግን ሙሴን አል​ሰ​ሙ​ትም፤ አን​ዳ​ንድ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ለነገ አስ​ቀሩ፤ እር​ሱም ተላ፤ ሸተ​ተም፤ ሙሴም ተቈ​ጣ​ቸው።

21 ሰውም ሁሉ ለየ​ራሱ ጥዋት ጥዋት ሰበ​ሰበ፤ ፀሐ​ይም በተ​ኰሰ ጊዜ ቀለጠ።

22 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ሁለት እጥፍ አድ​ር​ገው እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ሁለት ጎሞር እን​ጀራ ሰበ​ሰቡ፤ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ሁሉ መጥ​ተው ለሙሴ ነገ​ሩት።

23 ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረ​ፍት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ሰን​በት ነው፤ ነገ የም​ት​ጋ​ግ​ሩ​ትን ዛሬ ጋግሩ፤ የም​ት​ቀ​ቅ​ሉ​ት​ንም ቀቅሉ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ለነገ እን​ዲ​ጠ​በቅ አኑሩ” አላ​ቸው።

24 ሙሴም እንደ አዘዘ ለነገ አኖ​ሩት፤ አል​ሸ​ተ​ተም፤ ትልም አል​ሆ​ነ​በ​ትም።

25 ሙሴም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በት ዛሬ ነውና ብሉት፤ ዛሬ በሜዳ አታ​ገ​ኙ​ትም።

26 ስድ​ስት ቀን ልቀ​ሙት፤ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን ሰን​በት ነው፤ በእ​ርሱ አይ​ገ​ኝም” አለ።

27 በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ከሕ​ዝቡ አን​ዳ​ንድ ሰዎች ሊለ​ቅሙ ወጡ፤ ግን ምንም አላ​ገ​ኙም።

28 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ትእ​ዛ​ዞ​ች​ንና ሕጎ​ችን ለመ​ስ​ማት እስከ መቼ እንቢ ትላ​ላ​ችሁ?

29 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በ​ትን እንደ ሰጣ​ችሁ እዩ፤ ስለ​ዚህ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን የሁ​ለት ቀን እን​ጀራ ሰጣ​ችሁ፤ ሰው ሁሉ በቤቱ ይቀ​መጥ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ማንም ከቤቱ አይ​ሂድ” አለው።

30 ሕዝ​ቡም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ዐረፈ።

31 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ስሙን መና ብለው ጠሩት፤ እር​ሱም እንደ ድን​ብ​ላል ዘር ነጭ ነው፤ ጣዕ​ሙም እንደ ማር እን​ጀራ ነው።

32 ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ነገር ይህ ነው፦ ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ኋ​ችሁ ጊዜ በም​ድረ በዳ ያበ​ላ​ኋ​ች​ሁን እን​ጀራ ያዩ ዘንድ ከእ​ርሱ አንድ ጎሞር ሙሉ ለልጅ ልጆ​ቻ​ችሁ ይጠ​በቅ” አለ።

33 ሙሴም አሮ​ንን፥ “አንድ የወ​ርቅ መሶብ ወስ​ደህ ጎሞር ሙሉ መና አግ​ባ​በት፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ይጠ​በቅ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አኑ​ረው” አለው።

34 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ ይጠ​በቅ ዘንድ አሮን በም​ስ​ክሩ ፊት አኖ​ረው።

35 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​ባት ምድር እስ​ከ​ሚ​መጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ።

36 ወደ ፊኒ​ቆ​ንም ምድር እስ​ኪ​መጡ ድረስ መና በሉ። ጎሞ​ርም የሦ​ስት ላዳን መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል ነው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos