ዘፀአት 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 በጎሞርም በሰፈሩት ጊዜ እጅግ ለሰበሰበ አልተረፈውም፤ ጥቂትም ለሰበሰበ አልጐደለበትም፤ ሁሉም እያንዳንዱ ሰው ለየቤቱ ሰበሰበ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 የሰበሰቡትን በጎሞር በሰፈሩ ጊዜ፣ ብዙ የሰበሰበ አላተረፈም፤ ጥቂትም የሰበሰበ አልጐደለበትም፤ እያንዳንዱ የሰበሰበው የሚያስፈልገውን ያህል ሆነ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 በዖሜርም በሰፈሩት ጊዜ ብዙ የሰበሰበው አልተረፈውም ጥቂት የሰበሰበውም አላነሰውም፤ የሰበሰቡት እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 በሰፈሩትም ጊዜ ብዙ የሰበሰበው አልተረፈውም፤ ጥቂትም የሰበሰበ አላነሰበትም፤ እያንዳንዱ የሰበሰበው ልክ የሚበቃውን ያኽል ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 በጎሞርም በሰፈሩት ጊዜ እጅግ ለለቀመ አልተረፈውም ጥቂትም ለለቀመ አልጎደለበትም፤ ሁሉ እያንዳንዱ የሚበላውን ያህል ለቀመ። Ver Capítulo |