ዘዳግም 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በምድር ፊት ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መርጦሃልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ስለ ሆንህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ፣ ርስትም እንድትሆንለት በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ መረጠህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለጌታ አምላክህ አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች ሁሉ፥ ጌታ አምላክህ ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ እንድትሆን መረጠህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ እግዚአብሔር አምላክህ የራሱ ወገን አድርጎ የመረጠህ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ በምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች ሁሉ አንተ ለእርሱ የተለየህ ምርጥ ሕዝብ እንድትሆን አድርጎሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በምድር ፊት ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መረጠህ። |
ለራሳቸውና ለልጆቻቸውም ሴቶች ልጆቻቸውን ወስደዋል፤ የተቀደሰውንም ዘር ከምድር አሕዛብ ጋር ደባልቀዋል፤ አስቀድሞም አለቆቹና ሹሞቹ በዚህ መተላለፍ መጀመሪያ ሆነዋል” አሉኝ።
ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፤ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ፥ ከማዕዘንዋም የጠራሁህ ነህና፦ አንተ ባሪያዬ ነህ፤ መርጬሃለሁ፤ አልጥልህም፤ ያልሁህ ሆይ፥
በእርስዋም ዘንድ ዐሥረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃጠላል፤ ቅጠሎቻቸውም በረገፉ ጊዜ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሁነው ይቀራሉ።
እግዚአብሔር፥ “የተቤዣቸው፥ የተቀደሰ ሕዝብ” ብለው ይጠሩአቸዋል፤ አንቺም፥ “የተተወች ያይደለች የተወደደች ቅድስት ከተማ” ትባያለሽ።
እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረ፤ የቡቃያው በኵራትም ነበረ፤ የበሉት እንደ በደለኞች ይቈጠራሉ፤ ክፉም ነገር ያገኛቸዋል፤ ይላል እግዚአብሔር።”
እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤልን ቤት በመረጥሁበት፥ ለያዕቆብም ቤት ዘር በታወቅሁበት ቀን፥ በግብፅም ምድር በተገለጥሁላቸው ጊዜ እጄን አንሥቼ፦ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ አልኋቸው።
ነገር ግን እናንተ፦ ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ ትወርሱአትም ዘንድ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ አልኋችሁ፤ እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።
“እኔ ከምድር አሕዛብ ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኀጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።”
እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።
የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መረጣቸው፤ ወገኖቹንም በተሰደዱበት በምድረ ግብፅ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ ከዚያም ከፍ ባለ ክንዱ አወጣቸው።
ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ እግዚአብሔር አንተን መርጦአልና።
የበከተዉን ሁሉ አትብሉ፤ ይበላው ዘንድ በሀገርህ ደጅ ለተቀመጠ መጻተኛ ወይም ለባዕድ ስጠው፤ አንተ ለአምላካህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ነህና፥ የፍየሉን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።
ከአሕዛብ ሁሉ በላይ ትሆን ዘንድ፥ እርሱም እንደ ተናገረ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ትሆን ዘንድ ታላቅ ስምን፥ ምስጋናና ክብርንም አደረገልህ።”
የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትሰማ፥ በመንገዱም ብትሄድ፥ እግዚአብሔር ለአባቶችህ እንደ ማለ ለእርሱ የተቀደሰ ሕዝብ አድርጎ ያቆምሃል።
መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤
እግዚአብሔር ለእርሱ ሕዝብ ያደርጋችሁ ዘንድ ተቀብሎአችኋልና፥ እግዚአብሔር ስለ ታላቅ ስሙ ሕዝቡን አይተውም።