ዘሌዋውያን 20:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ነገር ግን እናንተ፦ ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ ትወርሱአትም ዘንድ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ አልኋችሁ፤ እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 እናንተ ግን፣ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ ማርና ወተት የምታፈስሰውን አገር ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ” አልኋችሁ፤ ከአሕዛብ የለየኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ነገር ግን እኔ እንዲህ አልኋችሁ፦ ‘ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እንድትወርሱአትም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ።’ እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ ጌታ አምላካችሁ ነኝ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ነገር ግን ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እንድትወርሱ እሰጣችኋለሁ፤ ከሌሎች ሕዝቦች እንድትለዩ ያደረግኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ነገር ግን እናንተን፦ ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ ትወርሱአትም ዘንድ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ አልኋችሁ። እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ። Ver Capítulo |
ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ! አባቶቻችንን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በባሪያህ በሙሴ እጅ እንደ ተናገርህ ርስት ይሆኑህ ዘንድ ከምድር አሕዛብ ሁሉ ለይተሃቸዋልና።” ያንጊዜም ሰሎሞን ሥራውን በጨረሰ ጊዜ ስለዚያ ቤት እንዲህ ሲል ተናገረ። “እግዚአብሔር በሰማይ ፀሐይን አሳየ፤ እግዚአብሔር በጨለማ ውስጥ እንደሚኖር ተናገረ፤ ቤቴን ሥራ፤ በመታደስም ለመኖር ለራስህ ጥሩ ቤትን ሥራ፤” ይህችስ በመሐልይ መጽሐፍ የተጻፈች አይደለምን?