ዘዳግም 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥ አስማተኛም፥ መተተኛም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመካከልህ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ ሟርተኛ ወይም መተተኛ፣ ሞራ ገላጭ፣ ጠንቋይ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመካከልህ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ ሟርተኛ፥ ወይም መተተኛ፥ ሞራ ገለጭ፥ ጠንቋይ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ከመካከልህ ወንድ ልጁን፥ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ አይኑር፤ ወይም አስማተኛ፥ ሟርተኛ፥ ጠንቋይ፥ መተተኛ አይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድ ልጁን ሴት ልጁን በእሳት የሚያሳልፍ፥ ምዋርተኛም፥ ሞራ ገላጭም፥ |
ነገር ግን በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ ደግሞም እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብ ርኵሰት ልጁን በእሳት ሠዋው።
የገባላቸውንም ቃል ኪዳን ሁሉ አልጠበቁም። ከንቱ ነገርንም ተከተሉ፤ ከንቱም ሆኑ፤ እንደ እነርሱም እንዳይሠሩ ያዘዛቸውን በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ተከተሉ።
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም በእሳት ሥዉአቸው፤ ምዋርተኞችና አስማተኞችም ሆኑ፤ ያስቈጡትም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር ለማድረግ ራሳቸውን ሸጡ።
ልጁንም በእሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ በእግዚአብሔርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ፤ ኣስቈጣውም።
ደግሞም ካህኑ ኬልቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈውን የሕጉን ቃል ያጸና ዘንድ፥ መናፍስት ጠሪዎቹንና ጠንቋዮቹን ተራፊምንና ጣዖታትንም በይሁዳ ሀገርና በኢየሩሳሌም የተገኘውን ርኵሰት ሁሉ ኢዮስያስ አስወገደ።
እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኀጢአት፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪን ጠየቀ።
ደግሞም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ለምስሉ ሠዋ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብም ክፉ ልማድ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ።
በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ። መተተኛም ነበረ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገርን አደረገ።
በክፉ ምክርሽ ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፥ ከዋክብትንም የሚመለከቱ ይነሡ፤ ያድኑሽም፤ ምን እንደሚመጣብሽም ይንገሩሽ፤
ከምድራችሁ እንዲያርቁአችሁ፥ እኔም እንዳሳድዳችሁ፥ እናንተም እንድትጠፉ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና።
እናንተ ግን፦ ለባቢሎን ንጉሥ አትገዙም የሚሉአችሁን የሐሰት ነቢያቶቻችሁንና ምዋርተኞቻችሁን፥ ሕልም ዐላሚዎቻችሁንና ባለ ራእዮቻችሁን፥ መተተኞቻችሁንም አትስሙ፤
ይሁዳን ወደ ኀጢአት እንዲያገቡት፥ ይህን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን መሠዊያዎች ለበዓል ሠሩ።”
እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያለችውን የቶፌትን መሥዊያዎች ሠርተዋል።
“ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች አትሂዱ፤ እንዳትረክሱባቸውም አትፈልጉአቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
“እነርሱን ተከትሎ ያመነዝር ዘንድ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን የሚከተል ሰው ቢኖር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይች አጠፋዋለሁ።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ብዙዎች አስማተኞችም መጽሐፎቻቸውን እየሰበሰቡ እያመጡ በሕዝቡ ሁሉ ፊት በእሳት ያቃጥሉ ነበር፤ ያቃጠሏቸው የመጽሐፎች ዋጋም አምሳ ሺህ ብር ነበር።
በዚያችም ከተማ ሲሞን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ የሰማርያ ሰዎችንም ያስት ነበር፤ ሰውየዉ ሥራየኛ ነበር፤ ራሱንም ታላቅ ያደርግ ነበር።
ጣዖት ማምለክ፥ ሥራይ ማድረግ፥ መጣላት፥ ኵራት፥ የምንዝር ጌጥ፥ ቅናት፥ ቍጣ፥ ጥርጥር፥ ፉክክር፥ ምቀኝነት፥ መጋደል፥ ስካር ይህንም የመሰለ ሁሉ ነው።
ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንዲሁ አታድርግ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአምላኮቻቸው በእሳት ስለሚያቃጥሉ አሕዛብ ለአምላኮቻቸው የሚያደርጉትን ርኩስ ነገር እግዚአብሔር ይጠላልና።
ኀጢኣት እንደ ምዋርተኝነት ናትና አምልኮተ ጣዖትም ደዌንና ኀዘንን ያመጣል። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ” አለው።
ሳሙኤል ግን ሞቶ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ አልቅሰውለት ነበር፤ በከተማውም በአርማቴም ቀብረውት ነበር። ሳኦልም መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር አጥፍቶ ነበር።
ሳኦልም ብላቴኖቹን፥ “ወደ እርስዋ ሄጄ እጠይቅ ዘንድ መናፍስትን የምትጠራ ሴት ፈልጉልኝ” አላቸው፤ ብላቴኖቹም፥ “እነሆ፥ መናፍስትን የምትጠራ አንዲት ሴት በዓይንዶር አለች” አሉት።
ሳኦልም መልኩን ለውጦ፥ ሌላ ልብስም ለብሶ ሄደ፤ ሁለትም ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ በሌሊትም ወደ ሴቲቱ መጡ። ሳኦልም፥ “እባክሽ በመናፍስት አምዋርቺልኝ፤ የምልሽንም አስነሽልኝ” አላት።
ሴቲቱም፥ “እነሆ፥ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር እንዳጠፋ ሳኦል ያደረገውን ታውቃለህ፤ ስለምን እኔን ለማስገደል ለነፍሴ ወጥመድ ታደርጋለህ?” አለችው።