ሐዋርያት ሥራ 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ኀጢአታችሁ ይሰረይላችሁ ዘንድ ንስሓ ግቡ፥ ተመለሱም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኀጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ፤ ተመለሱም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስላችሁ ንስሓ ገብታችሁ ወደ ጌታ ተመለሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም። |
አድርገህልኛልና ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ፥ በጻድቃንህም ዘንድ መልካም ነውና ምሕረትህን ተስፋ አደርጋለሁ።
እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ ወደ ጽዮንም በደስታና በሐሤት ይመጣሉ፤ የዘለዓለምም ክብር በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፤ ኀዘንና ልቅሶም ይወገዳሉ።
እነዚህ ሕዝቦች በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ ልባቸውን አደንድነዋልና፥ ጆሮአቸውንም ደፍነዋልና፥ ዐይኖቻቸውንም ጨፍነዋልና።
እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድም ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
ዘራቸው በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ያውቃል፤
ምናልባት የይሁዳ ቤት ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ዘንድ፥ እኔም በደላቸውንና ኀጢአታቸውን ይቅር እል ዘንድ፥ እኔ አደርግባቸዋለሁ ያልሁትንና ያሰብሁትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል።”
በዚያ ወራት በዚያም ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እነዚህን በምድር የተረፉትን ይቅር እላቸዋለሁና የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤ አይኖርምም፤ የይሁዳም ኀጢአት ይፈለጋል፥ ምንም አይገኝም።
እኔ ሕያው ነኝና ኀጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኀጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ተመለሱ፤ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፥ ቍጣው የዘገየ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።”
በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዐይናቸውንም ጨፍነዋል፤’ የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።
ይህንም በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፥ “እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሓን ሰጣቸው እንጃ” እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
ከቤተ ክርስቲያንም በተላኩ ጊዜ ወደ ሰማርያና ወደ ፊንቄ ደርሰው አሕዛብ ወደ ሃይማኖት እንደ ተመለሱ ነገሩቸአቸው፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው።
እርሱም በምድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎችን ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖሩባትም ዘንድ ዘመንንና ቦታን ወስኖ ሠራላቸው።
ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፥ “ንስሓ ግቡ፤ ሁላችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ ኀጢአታችሁም ይሰረይላችኋል፤ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ትቀበላላችሁ።
በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ወደ እኔም እንዳይመለሱና ይቅር እንዳልላቸው የዚህ ሕዝብ ልባቸው ደንድኖአልና፥ ጆሮአቸውም ደንቁሮአልና፥ ዐይናቸውንም ጨፍነዋልና’።
ከእግዚአብሔር ዘንድም የይቅርታ ዘመን ይመጣል። አስቀድሞ የመረጠውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ይልክላችኋል።
እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እስከ ተናገረው የመደራጀት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባል።
ወንድሞቻችን፥ እና ዐዋቂዎች ነን እንዳትሉ ይህን ምሥጢር ልታውቁ እወዳለሁ፦ አሕዛብ ሁሉ እስኪገቡ ድረስ ከእስራኤል እኩሌቶችን የልብ ድንቍርና አግኝቶአቸዋልና።
ደግሞም “ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሓን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው ወደ አእምሮ ይመለሳሉ፤” ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ።
እንግዲህ አንፍራ፤ ወደ ዕረፍቱም እንድንገባ ትእዛዙን አንተው፤ ከእናንተም ምንአልባት በተለመደ ስሕተት የሚገኝና የሚጸና ቢኖር ወደ ዕረፍቱ እንዲገባ የሚተዉት አይምሰለው።
እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ! በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
እንባዎችንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ያብሳል፤ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ ሐዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ የቀደመው ሥርዐት አልፎአልና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።