Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሰቈቃወ 3:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ኖን። መን​ገ​ዳ​ች​ንን እን​መ​ር​ም​ርና እን​ፈ​ትን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​መ​ለስ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 መንገዳችንን እንመርምር፤ እንፈትን፤ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ኖን። መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 አካሄዳችንን መርምረን፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ኖን። መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 3:40
22 Referencias Cruzadas  

በሃ​ይ​ማ​ኖት ጸን​ታ​ችሁ እንደ ሆነ ራሳ​ች​ሁን መር​ምሩ፤ እና​ንተ ራሳ​ች​ሁን ፈትኑ፤ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ዳለ አታ​ው​ቁ​ምን? እን​ዲህ ካል​ሆነ ግን እና​ንተ የተ​ና​ቃ​ችሁ ናችሁ።


ተቈጡ፥ ነገር ግን አት​በ​ድሉ፤ በመ​ኝ​ታ​ችሁ ሳላ​ችሁ በል​ባ​ችሁ የም​ታ​ስ​ቡት ይታ​ወ​ቃ​ችሁ።


ክፉ ሰው መን​ገ​ዱን፥ በደ​ለ​ኛም ዐሳ​ቡን ይተው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ፤ እር​ሱም ይም​ረ​ዋል፤ እርሱ ብዙ በደ​ላ​ች​ሁን ይተ​ው​ላ​ች​ኋ​ልና።


በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ በማ​ለዳ ወደ እኔ ይገ​ሰ​ግ​ሳሉ፤ እን​ዲ​ህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​መ​ለስ፤ እርሱ ሰብ​ሮ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይፈ​ው​ሰ​ናል፤ እርሱ መት​ቶ​ና​ልና፥ እር​ሱም ይጠ​ግ​ነ​ናል።


አሁ​ንም ሰው ራሱን መር​ም​ሮና አን​ጽቶ ከዚህ ኅብ​ስት ይብላ፤ ከዚ​ህም ጽዋ ይጠጣ።


እኛ በራ​ሳ​ችን ብን​ፈ​ርድ ኖሮ ባል​ተ​ፈ​ረ​ደ​ብ​ንም ነበር።


እንደ ንጉ​ሡም ትእ​ዛዝ መል​እ​ክ​ተ​ኞቹ እን​ዲህ የሚ​ለ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ደብ​ዳቤ ይዘው ወደ እስ​ራ​ኤ​ልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ፈጥ​ነው ሄዱ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ ወዳ​መ​ለጠ ቅሬ​ታ​ችሁ እን​ዲ​መ​ለስ ወደ አብ​ር​ሃ​ምና ወደ ይስ​ሐቅ ወደ ያዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለሱ።


ከሠ​ራው ሁሉ በደል አይቶ ተመ​ል​ሶ​አ​ልና ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸርና መሓሪ ነውና፥ ወደ እር​ሱም ብን​መ​ለስ ፊቱን ከእኛ አያ​ዞ​ር​ምና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብት​መ​ለሱ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ በማ​ረ​ኩ​አ​ቸው ፊት ምሕ​ረ​ትን ያገ​ኛሉ፤ ደግ​ሞም ወደ​ዚ​ህች ምድር ይመ​ል​ሳ​ቸ​ዋል።”


ይህም ሁሉ ነገር በመ​ጨ​ረ​ሻው ዘመን ይደ​ር​ስ​ብ​ሃል፤ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትመ​ለ​ሳ​ለህ፤ ቃሉ​ንም ትሰ​ማ​ለህ።


አስ​ቀ​ድሜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በደ​ማ​ስቆ ላሉት፥ ለይ​ሁዳ አው​ራ​ጃ​ዎ​ችም ሁሉ ነገ​ር​ኋ​ቸው፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ንስሓ ገብ​ተው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ለሱ ዘንድ፥ ለን​ስ​ሓ​ቸ​ውም የሚ​ገባ ሥራን ይሠሩ ዘንድ አስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ቸው።


ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ሰ​ቢ​ያው ነው።


እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥ ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios