Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 17:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እር​ሱም በም​ድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎ​ችን ሁሉ ከአ​ንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖ​ሩ​ባ​ትም ዘንድ ዘመ​ን​ንና ቦታን ወስኖ ሠራ​ላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ወገን ፈጥሮ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ አደረገ፤ የዘመናቸውን ልክና የመኖሪያ ስፍራቸውንም ዳርቻ ወሰነላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26-27 ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፤ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም አደረገ፤ የተወሰኑ ዘመኖችንና የሚኖሩባቸውንም ቦታዎች መደበላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26-27 ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 17:26
20 Referencias Cruzadas  

አዳ​ምም ለሚ​ስቱ “ሔዋን” ብሎ ስም አወጣ፤ የሕ​ያ​ዋን ሁሉ እናት ናትና።


በም​ድር ሁሉ ላይ የተ​በ​ተኑ የኖኅ ልጆች እነ​ዚህ ሦስቱ ናቸው።


አሕ​ዛ​ብን ያቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ቸ​ዋል፤ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ልም፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ያፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ልም።


በም​ድር ላይ አንድ ቀንም እንኳ ቢኖር፤ ወሮ​ቹም በአ​ንተ ዘንድ የተ​ቈ​ጠሩ ናቸው፤ ዘመ​ኑ​ንም ወስ​ነህ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም ከዚያ አያ​ል​ፍም።


እና​ንተ የከ​ተ​ሞች በሮች ሆይ፥ ወዮ በሉ፤ እና​ን​ተም ከተ​ሞች ሆይ፥ ደን​ግጡ፥ ጩኹም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሆይ፥ ሁላ​ች​ሁም ቀል​ጣ​ች​ኋል፤ ጢስ ከሰ​ሜን ይወ​ጣ​ልና፥ እን​ግ​ዲ​ህም አት​ኖ​ሩ​ምና።


እር​ሱም ዕጣ ጣለ​ባ​ቸው፤ እጁም ከፈ​ለ​ች​ላ​ቸው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሰ​ማ​ሩ​ባ​ታል፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በው​ስ​ጥ​ዋም ያር​ፉ​ባ​ታል።


የሚ​ና​ገሩ ከሆነ ከጥ​ንት ጀምሮ ይህን ምስ​ክ​ር​ነት ያደ​ረገ ማን እንደ ሆነ በአ​ን​ድ​ነት ያውቁ ዘንድ ይቅ​ረቡ። ያሳ​የ​ሁም የተ​ና​ገ​ር​ሁም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አም​ላ​ክና መድ​ኀ​ኒት ነኝ፥ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


ምድ​ሪ​ቱን፥ በም​ድር ፊት ላይ ያሉ​ትን ሰዎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን በታ​ላቅ ኀይ​ሌና በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችው ክንዴ ፈጥ​ሬ​አ​ለሁ፤ ለዐ​ይ​ኔም መል​ካም ለሆ​ነው እሰ​ጣ​ታ​ለሁ።


ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?


ከዚ​ህም ሁሉ ጋር መል​ካም ሥራን እየ​ሠራ ከሰ​ማይ ዝና​ምን፥ ፍሬ የሚ​ሆ​ን​በ​ት​ንም ወራት ሲሰ​ጠን፥ ልባ​ች​ን​ንም በመ​ብ​ልና በደ​ስታ ሲሞ​ላው ራሱን ያለ ምስ​ክር አል​ተ​ወም።”


ከጥ​ንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የታ​ወቀ ነው።


ሁሉ በአ​ዳም እን​ደ​ሚ​ሞት እን​ዲሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉ ሕያ​ዋን ይሆ​ናሉ።


መጀ​መ​ሪ​ያው ሰው ከመ​ሬት የተ​ገኘ መሬ​ታዊ ነው፤ ሁለ​ተ​ኛው ሰው ከሰ​ማይ የወ​ረደ ሰማ​ያዊ ነው።


እኛስ እን​ዲህ ያለ​ውን ታላቅ መዳን ቸል ብን​ለው እን​ዴት እና​መ​ል​ጣ​ለን? ይህ በጌታ በመ​ጀ​መ​ሪያ የተ​ነ​ገረ ነበ​ረና የሰ​ሙ​ትም ለእኛ አጸ​ኑት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos