ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፥ “ከእናንተ ጋር ያሉ እንግዶች አማልክትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ንጹሓንም ሁኑ፤ ልብሳችሁንም እጠቡ፤
ሐዋርያት ሥራ 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ለጣዖት ከሚሠዋው፥ ከዝሙት፥ ሞቶ የተገኘውንና ደም ከመብላት እንዲርቁ፥ ለራሳቸው የሚጠሉትንም በወንድሞቻቸው ላይ እንዳያደርጉ እዘዙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይልቁን በጣዖት ከረከሰ ነገር፣ ከዝሙት ርኩሰት፣ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋ ከመብላትና ደም ከመመገብ እንዲርቁ ልንጽፍላቸው ይገባል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከጣዖት ርኩሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቆርጣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይልቅስ ‘ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብን አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ሳይታረድና ደሙም ሳይፈስ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምንም አትብሉ’ ብለን እንጻፍላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ። |
ያዕቆብም ለቤተ ሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፥ “ከእናንተ ጋር ያሉ እንግዶች አማልክትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ንጹሓንም ሁኑ፤ ልብሳችሁንም እጠቡ፤
የብር አማልክትን አታምልኩ፤ የወርቅ አማልክትንም አታምልኩ። የዕንጨትና የድንጋይ አምላክንም አታምልኩ፤ እንዲህ ያለ አምላክን ለእናንተ አታድርጉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፤ ዐይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?
እኔም፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ይህ አግባብ አይደለም፤ እነሆ ሰውነቴ አልረከሰችም፤ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ጥንብና አውሬ የሰበረውን ከቶ አልበላሁም፤ ርኵስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም” አልሁ።
“ከእናንተም ማንም ሰው ኀፍረተ ሥጋውን ይገልጥ ዘንድ ወደ ሥጋ ዘመዱ ሁሉ አይቅረብ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ለአማልክት የተሠዋውን፥ ሞቶ የተገኘውን፥ ደምንም አትብሉ፤ ከዝሙትም ራቁ፤ በራሳችሁ የምትጠሉትንም በወንድሞቻችሁ ላይ አታድርጉ፥ ከእነዚህ ሥራዎችም ሰውነታችሁን ብትጠብቁ በሰላም ትኖራላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”
ስለሚአምኑት አሕዛብ ግን እርም ከሆነውና ለጣዖታት ከሚሠዉት፥ ከዝሙት፥ ሞቶ የተገኘውንና ደምን ከመብላት እንዲከለከሉ እኛ አዝዘናል።”
አሁንም ከወንድሞች መካከል ዘማዊ፥ ወይም ገንዘብን የሚመኝ፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ፥ ወይም ዐመፀኛ፥ ወይም ተራጋሚ፥ ወይም ሰካራም፥ ወይም የሚቀማ ቢኖር እንደዚህ ካለ ሰው ጋር አንድ እንዳትሆኑ ጻፍሁላችሁ፥ እንደዚህ ካለው ሰው ጋር መብልም እንኳ አትብሉ፤
መብል ለሆድ ነው ፤ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ይሽራቸዋል፤ ሥጋችሁም ለእግዚአብሔር ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ እግዚአብሔርም ለሥጋችሁ ነው።
ከዝሙት ራቁ፤ ኀጢአት የሚሠራ ሰው ሁሉ ከሥጋው ውጭ ይሠራልና፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን ራሱ በሥጋው ላይ ኀጢአትን ይሠራል።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አያስቱአችሁ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ቀላጮች፥ ወይም በወንድ ላይ ዝሙትን የሚሠሩ፥ የሚሠሩባቸውም ቢሆኑ፤
ለጣዖታት ስለሚሠዉ መሥዋዕቶች ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን እናውቃለን፤ ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።
ወይም እንደ ገና ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔር ያሳዝነኝ ይሆናል፤ በድለው ንስሓ ላልገቡም ስለ ርኵስነታቸውና ስለ መዳራታቸው፥ ስለሚሠሩት ዝሙታቸውም ለብዙዎች አዝን ይሆናል።
የበከተዉን ሁሉ አትብሉ፤ ይበላው ዘንድ በሀገርህ ደጅ ለተቀመጠ መጻተኛ ወይም ለባዕድ ስጠው፤ አንተ ለአምላካህ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሕዝብ ነህና፥ የፍየሉን ጠቦት በእናቱ ወተት አትቀቅል።
መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለውም፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።
የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።
የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
ከሰማይም የሰማሁት ድምፅ እንደ ገና ሲናገረኝና “ሂድና በባሕርና በምድር ላይ ከሚቆመው መልአክ በእጁ ያለችውን የተከፈተችውን መጽሐፍ ውሰድ፤” ሲል ሰማሁ።
ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።
ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤
በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤
ሕዝቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎችን፥ በሬዎችንም፥ ጥጆችንም ወስደው እንዳገኙ በምድር ላይ አረዱ፤ ሕዝቡም ከደሙ ጋር በሉ።
ለሳኦልም፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ ከደሙ ጋር በመብላታቸው እግዚአብሔርን በደሉ” ብለው ነገሩት። ሳኦልም በጌቴም “ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አቅርቡልኝ” አላቸው።