Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በእነዚህ መቅሠፍቶች ሳይገደሉ የቀሩት ሰዎች አሁንም ከእጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትን እንዲሁም ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ የማይችሉትን፣ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከናስ፣ ከድንጋይና ከዕንጨት የተሠሩትን ጣዖቶች ማምለክ አልተዉም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ ለአጋንንትና ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶችም መስገድን አልተዉም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በእነዚህ መቅሠፍቶች ከሞት የተረፉት የሰው ዘር ከእጃቸው ሥራ ተመልሰው ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትንና ከወርቅ፥ ከብር፥ ከናስ፥ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩ ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ የማይችሉትን ጣዖቶች ማምለክንም አልተዉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ሥራ ንስሐ አልገቡም፤

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 9:20
43 Referencias Cruzadas  

ከሞ​ትሁ በኋላ ፈጽ​ማ​ችሁ እን​ድ​ት​ረ​ክሱ፥ ካዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም መን​ገድ ፈቀቅ እን​ድ​ትሉ አው​ቃ​ለ​ሁና። በእ​ጃ​ች​ሁም ሥራ ታስ​ቈ​ጡት ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገ​ኛ​ች​ኋል።”


ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሓ አልገቡም።


መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥


አሁን ግን እን​ደ​ም​ታ​ዩ​ትና እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙት ይህ ጳው​ሎስ ኤፌ​ሶ​ንን ብቻ ሳይ​ሆን መላ​ውን እስ​ያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚ​ሠ​ሩ​ት​ንም ሁሉ አማ​ል​ክት አይ​ደ​ሉም አላ​ቸው።


ያን​ጊ​ዜም የጥጃ ምስል ሠሩ፤ ለጣ​ዖ​ቱም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ በእ​ጃ​ቸው ሥራም ደስ አላ​ቸው።


ስለ ክፋ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ፥ እኔን ስለ ተዉ፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት ስለ ሠዉ፥ ለእ​ጃ​ቸ​ውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍር​ዴን በእ​ነ​ርሱ ላይ እና​ገ​ራ​ለሁ።


ወይም እንደ ገና ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ዝ​ነኝ ይሆ​ናል፤ በድ​ለው ንስሓ ላል​ገ​ቡም ስለ ርኵ​ስ​ነ​ታ​ቸ​ውና ስለ መዳ​ራ​ታ​ቸው፥ ስለ​ሚ​ሠ​ሩት ዝሙ​ታ​ቸ​ውም ለብ​ዙ​ዎች አዝን ይሆ​ናል።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀ​ትን አጥ​ቶ​አል፥ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ሐሰ​ተ​ኞች ጣዖ​ታ​ትን ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የላ​ቸ​ው​ምና።


እን​ግ​ዲህ እኛ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመ​ዶች ከሆን በሰው ዕው​ቀ​ትና ብል​ሀት በተ​ቀ​ረጸ በድ​ን​ጋ​ይና በብር፥ በወ​ር​ቅም አም​ላ​ክ​ነ​ቱን ልን​መ​ስ​ለው አይ​ገ​ባም።


ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ መጥቶላችሁ ነበርና፤ አላመናችሁበትም፤ ቀራጮችና ጋለሞቶች ግን አመኑበት፤ እናንተም ይህን አይታችሁ ታምኑበት ዘንድ በኋላ ንስሐ አልገባችሁም።


ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ታጠፉ ዘንድ፥ በም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል መረ​ገ​ሚ​ያና መሰ​ደ​ቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመ​ቀ​መጥ በገ​ባ​ች​ሁ​ባት በግ​ብፅ ምድር ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት በማ​ጠ​ና​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ለምን ታስ​ቈ​ጡ​ኛ​ላ​ችሁ?


ትገ​ዙ​ላ​ቸ​ውና ትሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ከ​ተሉ፤ ክፉም እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ በእ​ጃ​ችሁ ሥራ አታ​ስ​ቈ​ጡኝ።


አቤቱ! ዐይ​ኖ​ችህ ለሃ​ይ​ማ​ኖት አይ​ደ​ሉ​ምን? አንተ ቀሥ​ፈ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን አላ​ዘ​ኑም፤ ቀጥ​ቅ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ነገር ግን ተግ​ሣ​ጽን እንቢ አሉ፤ ፊታ​ቸ​ውን ከድ​ን​ጋይ ይልቅ አጠ​ን​ክ​ረ​ዋል፤ ይመ​ለ​ሱም ዘንድ እንቢ አሉ።


እር​ሻ​ዎ​ች​ንም ዘሩ፥ ወይ​ኖ​ች​ንም ተከሉ፥ የእ​ህ​ል​ንም ሰብል አደ​ረጉ።


በእ​ጃ​ቸው ሥራ ሁሉ ሊያ​ስ​ቈ​ጡኝ ትተ​ው​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት አጥ​ነ​ዋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋ​ምም።


በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ሁሉ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ትታ​ች​ሁ​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ዐጥ​ና​ች​ኋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፥ አይ​ጠ​ፋ​ምም።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ​ደለ ለአ​ጋ​ን​ንት፥ ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸ​ውም አማ​ል​ክት፥ ድን​ገት ለተ​ገኙ ለማ​ይ​ሠ​ሩና ለማ​ይ​ጠ​ቅሙ አማ​ል​ክት፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸው አማ​ል​ክት ሠዉ።


አራተኛውም ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰዎችንም በእሳት ልታቃጥል ተሰጣት።


አና​ጢ​ውም አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን፥ በመ​ዶ​ሻም የሚ​ያ​ሳ​ሳ​ውን መስፍ መች​ውን አጽ​ናና፤ ስለ ማጣ​በቅ ሥራ​ውም፥ “መል​ካም ነው” አለ፤ እን​ዳ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ስም በች​ን​ካር አጋ​ጠ​መው።


ምድ​ራ​ቸ​ውም በእ​ጆ​ቻ​ቸው በሠ​ሩ​አ​ቸው ጣዖ​ታት ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በጣ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለሠ​ሩ​አ​ቸው ይሰ​ግ​ዳሉ።


ዳግ​መ​ኛም ንጉሡ አካዝ ፈጽሞ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራቀ።


መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሞ ተከ​ት​ለው ላመ​ነ​ዘ​ሩ​ባ​ቸው ለሰ​ይ​ጣ​ናት አይ​ሠዉ። ይህ ለእ​ነ​ርሱ ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።”


በዚ​ያም የማ​ያ​ዩ​ትን፥ የማ​ይ​ሰ​ሙ​ት​ንም፥ የማ​ይ​በ​ሉ​ት​ንም፥ የማ​ያ​ሸ​ቱ​ት​ንም፥ በሰው እጅ ከእ​ን​ጨ​ትና ከድ​ን​ጋይ የተ​ሠ​ሩ​ትን ሌሎች አማ​ል​ክት ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ።


የተቀረጹትን ምስሎችህንና ሐውልቶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ለእጅህም ሥራ ከእንግዲህ ወዲህ አትሰግድም፥


የፈረሶቹ ሥልጣን በአፋቸውና በጅራታቸው ነውና፥ ጅራታቸው እባብን ይመስላልና፥ ራስም አላቸው፤ በእርሱም ይጐዳሉ።


ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቍጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios