Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “ነገር ግን ሕይወቱ፣ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን ደም ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፥ ምክንያቱም በደም ውስጥ ሕይወት አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ነገር ግን በደሙ ውስጥ ሕይወት ስላለ ደም ያለበትን ሥጋ አትብሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 9:4
15 Referencias Cruzadas  

ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ና​ች​ሁ​ንም ወደ ጣዖ​ቶ​ቻ​ችሁ ታነ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ደም​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በውኑ ምድ​ሪ​ቱን ትወ​ር​ሳ​ላ​ች​ሁን?


“በተ​ራራ ላይ አት​ብሉ፤ አት​ር​ከሱ፥ በወ​ፍም አታ​ሟ​ርቱ።


ስብና ደም እን​ዳ​ት​በሉ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።”


በመ​ኖ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ሁሉ የወፍ ወይም የእ​ን​ስሳ ደም ቢሆን አት​ብሉ።


ነገር ግን ለጣ​ዖት ከሚ​ሠ​ዋው፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደም ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ርቁ፥ ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ እን​ዳ​ያ​ደ​ርጉ እዘ​ዙ​አ​ቸው።


ሁላ​ችን ከተ​ሰ​በ​ሰ​ብን በኋላ በአ​ንድ ቃል በየን፤ አንድ ሆነ​ንም ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ እና​ንተ የም​ን​ል​ካ​ቸ​ውን ሰዎች መረ​ጥን።


ለአ​ማ​ል​ክት የተ​ሠ​ዋ​ውን፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ውን፥ ደም​ንም አት​ብሉ፤ ከዝ​ሙ​ትም ራቁ፤ በራ​ሳ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ አታ​ድ​ርጉ፥ ከእ​ነ​ዚህ ሥራ​ዎ​ችም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ብት​ጠ​ብቁ በሰ​ላም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”


ደሙን ግን እንደ ውኃ በም​ድር ላይ አፍ​ስ​ሱት እንጂ አት​ብ​ሉት።


ደምን እን​ዳ​ት​በላ ተጠ​ን​ቀቅ፤ ደሙ ነፍሱ ነውና፥ ነፍ​ስም ከሥጋ ጋር አይ​በ​ላ​ምና።


የበ​ከ​ተ​ዉን ሁሉ አት​ብሉ፤ ይበ​ላው ዘንድ በሀ​ገ​ርህ ደጅ ለተ​ቀ​መጠ መጻ​ተኛ ወይም ለባ​ዕድ ስጠው፤ አንተ ለአ​ም​ላ​ካህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ ነህና፥ የፍ​የ​ሉን ጠቦት በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።


ነገር ግን ደሙን በም​ድር ላይ እንደ ውኃ አፍ​ስ​ሰው እንጂ አት​ብ​ላው።


እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም፤


ሕዝ​ቡም ወደ ምርኮ ሄዱ፤ በጎ​ችን፥ በሬ​ዎ​ች​ንም፥ ጥጆ​ች​ንም ወስ​ደው እን​ዳ​ገኙ በም​ድር ላይ አረዱ፤ ሕዝ​ቡም ከደሙ ጋር በሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos