Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 15:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ለአ​ማ​ል​ክት የተ​ሠ​ዋ​ውን፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ውን፥ ደም​ንም አት​ብሉ፤ ከዝ​ሙ​ትም ራቁ፤ በራ​ሳ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ አታ​ድ​ርጉ፥ ከእ​ነ​ዚህ ሥራ​ዎ​ችም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ብት​ጠ​ብቁ በሰ​ላም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ለጣዖት ከተሠዋ ነገር፣ ከደም፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከዝሙት ርኩሰት እንድትርቁ ነው። ከእነዚህ ዐይነት ነገሮች ብትርቁ ለእናንተ መልካም ነው። ደኅና ሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብ አትብሉ፤ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምም አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ብትጠበቁ መልካም ታደርጋላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 15:29
20 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ለጣ​ዖት ከሚ​ሠ​ዋው፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደም ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ርቁ፥ ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ እን​ዳ​ያ​ደ​ርጉ እዘ​ዙ​አ​ቸው።


ስለ​ሚ​አ​ም​ኑት አሕ​ዛብ ግን እርም ከሆ​ነ​ውና ለጣ​ዖ​ታት ከሚ​ሠ​ዉት፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደምን ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ከ​ለ​ከሉ እኛ አዝ​ዘ​ናል።”


ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤


ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።


የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነውና፤ ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፦ የሥጋ ሁሉ ሕይ​ወት ደሙ ነውና የሥ​ጋ​ውን ሁሉ ደም አት​ብሉ፤ የሚ​በ​ላ​ውም ሁሉ ተለ​ይቶ ይጥፋ አል​ኋ​ቸው።


ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፤


ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።


ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።


በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፤ በሌሎችም ኀጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽህና ጠብቅ።


ወድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ጽኑ፤ ታገሡ፤ በአ​ንድ ልብም ሁኑ፤ በሰ​ላም ኑሩ፤ የሰ​ላ​ምና የፍ​ቅር አም​ላ​ክም ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን።


ከእ​ና​ንተ ዘንድ በነ​በ​ር​ሁ​በት ጊዜም፥ ስቸ​ገር ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን አል​ተ​መ​ኘ​ሁም። ባል​በ​ቃ​ኝም ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከመ​ቄ​ዶ​ንያ መጥ​ተው አሙ​አ​ሉ​ልኝ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ እን​ዳ​ል​ከ​ብ​ድ​ባ​ችሁ በሁሉ ተጠ​ነ​ቀ​ቅሁ፤ ወደ ፊትም እጠ​ነ​ቀ​ቃ​ለሁ።


ከዚ​ህም በኋላ በሚ​ሸ​ኙት ጊዜ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢፈ​ቅድ እን​ደ​ገና እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ አሁን ግን የሚ​መ​ጣ​ውን በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላደ​ርግ እወ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው፤ ከኤ​ፌ​ሶ​ንም በመ​ር​ከብ ሄደ።


ሦስ​ተ​ኛ​ውም፥ “አቤቱ፥ ልከ​ተ​ል​ህን? ነገር ግን ሄጄ ቤተ ሰቦ​ችን ሁሉ እን​ድ​ሰ​ና​በት ፍቀ​ድ​ልኝ” አለው።


አይ​ሁ​ድም በዚህ ሰው ላይ በመ​ሸ​መቅ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን በዐ​ወ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ላክ​ሁት፤ ከሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ አንተ እን​ዲ​መ​ጡና በፊ​ትህ እን​ዲ​ፋ​ረ​ዱት አዝ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደኅና ሁን።”


ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤


ደሙን ግን እንደ ውኃ በም​ድር ላይ አፍ​ስ​ሱት እንጂ አት​ብ​ሉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios