ሐዋርያት ሥራ 12:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ አመለከታቸው፤ ከወኅኒ ቤትም እግዚአብሔር እንደ አወጣው ነገራቸው፤ “ይህንም ለያዕቆብና ለወንድሞች ሁሉ ንገሩ” አላቸው፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ዝም እንዲሉ በእጁ ጠቅሶ፣ ጌታ ከእስር ቤት እንዴት እንዳወጣው አስረዳቸው፣ “ስለ ሁኔታው ለያዕቆብና ለወንድሞች ንገሯቸው” አላቸው፤ ከዚያም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ጠቅሶ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣው ተረከላቸውና “ይህን ለያዕቆብና ለወንድሞቹ ንገሩ፤” አላቸው። ወጥቶም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ አመልክቶ ጌታ ከወህኒ ቤት እንዴት እንዳስወጣው አወራላቸውና “ይህን ነገር ለያዕቆብና ለቀሩት ምእመናን ንገሩ” አላቸው። ተለይቶአቸውም ወደ ሌላ ቦታ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ጠቅሶ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣው ተረከላቸውና፦ “ይህን ለያዕቆብና ለወንድሞቹ ንገሩ” አላቸው። ወጥቶም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ። |
በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን?” አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።
ወደ እነርሱ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜም እነርሱን ማነጋገር ተሳነው፤ በቤተ መቅደስም የተገለጠለት እንዳለ ዐወቁ፤ እንዲሁም ዲዳ ሆኖ በእጁ እያመለከታቸው ኖረ።
ከዚያም ወዲያ ጌታችን ኢየሱስ በአይሁድ መካከል በግልጥ አልተመላለሰም፤ ነገር ግን ለምድረ በዳ አቅራቢያ ወደ ሆነች ምድር፥ ኤፍሬም ወደምትባል ከተማ ሄደ፤ በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጠ።
ከዚህ በኋላም ጌታችን ኢየሱስ በገሊላ ይመላለስ ነበረ፤ ወደ ይሁዳ ምድርም ሊሄድ አልወደደም፤ አይሁድ ሊገድሉት ይሹ ነበርና።
ጳውሎስም ተነሥቶ ዝም እንዲሉ አዘዘና እንዲህ አላቸው፥ “እናንት የእስራኤል ሰዎችና እግዚአብሔርንም የምትፈሩ ሁሉ፥ ስሙ።
በዚያ የነበሩ አይሁድም እስክንድሮስ የሚባል አይሁዳዊ ሰውን ከመካከላቸው አስነሡ፤ እርሱም ተነሥቶ በእጁ ምልክት ሰጠና ለሕዝቡ ሊከራከርላቸው ወደደ።
በፈቀደለትም ጊዜ ጳውሎስ በደረጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳውሎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ተናገረ፤ እንዲህም አለ።
በዚያም ያሉት ወንድሞች ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ፤ አፍዩስ ፋሩስ እስከሚባለው ገበያና እስከ ሦስተኛው ማረፊያ ድረስ ወጥተው ተቀበሉን፤ ጳውሎስም ባያቸው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ልቡም ተጽናና።
ሰዎች ከያዕቆብ ዘንድ ከመምጣታቸው በፊት፥ ከአረማውያን ጋር ይበላ ነበርና፥ በመጡ ጊዜ ግን ተለያቸው፤ ከአይሁድ ወገን የሆኑትን ፈርቶአልና።
የሰጠኝንም ጸጋ ዐውቀው አዕማድ የሚሏቸው ያዕቆብና ኬፋ፥ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ፥ እነርሱም ወደ አይሁድ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን።