Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 13:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ጳው​ሎ​ስም ተነ​ሥቶ ዝም እን​ዲሉ አዘ​ዘና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎ​ችና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ ሁሉ፥ ስሙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ጳውሎስም ተነሥቶ በእጁ በመጥቀስ እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ ደግሞም እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፤ አድምጡ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጳውሎስም ተነሣና በእጁ ጠቅሶ እንዲህ አለ “የእስራኤል ሰዎችና እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ! ስሙ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለዚህ ጳውሎስ ተነሣና ሕዝቡን በእጁ ጠቀሰ፤ እንዲህም ሲል ተናገረ፤ “የእስራኤል ሰዎችና እግዚአብሔርን የምትፈሩ እናንተ አሕዛብ! ስሙ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ጳውሎስም ተነሣና በእጁ ጠቅሶ እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል ሰዎችና እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ፥ ስሙ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 13:16
29 Referencias Cruzadas  

እርሱ ግን ዝም እን​ዲሉ በእጁ አመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፤ ከወ​ኅኒ ቤትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ጣው ነገ​ራ​ቸው፤ “ይህ​ንም ለያ​ዕ​ቆ​ብና ለወ​ን​ድ​ሞች ሁሉ ንገሩ” አላ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።


“እና​ንተ ከአ​ብ​ር​ሃም ወገን የተ​ወ​ለ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ት​ፈሩ፥ ይህ የሕ​ይ​ወት ቃል ለእ​ና​ንተ ተል​ኮ​አል።


እር​ሱም ጻድ​ቅና ከነ​ቤተ ሰቡ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ነበር፤ ለሕ​ዝ​ቡም ብዙ ምጽ​ዋት ይሰጥ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።


ከጳ​ው​ሎ​ስም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “ይህ በሕ​ይ​ወት ሊኖር አይ​ገ​ባ​ው​ምና እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ከም​ድር አስ​ወ​ግ​ደው” እያሉ ጮሁ።


በፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም ጊዜ ጳው​ሎስ በደ​ረ​ጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅ​ግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳው​ሎስ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ።


በዚያ የነ​በሩ አይ​ሁ​ድም እስ​ክ​ን​ድ​ሮስ የሚ​ባል አይ​ሁ​ዳዊ ሰውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ነሡ፤ እር​ሱም ተነ​ሥቶ በእጁ ምል​ክት ሰጠና ለሕ​ዝቡ ሊከ​ራ​ከ​ር​ላ​ቸው ወደደ።


ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም ደፍ​ረው እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለእ​ና​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይገ​ባል፤ እንቢ ብት​ሉና ራሳ​ች​ሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የተ​ዘ​ጋጀ ባታ​ደ​ርጉ ግን እነሆ፥ ወደ አሕ​ዛብ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።


ነገር ግን በሕ​ዝብ ሁሉ ዘንድ እር​ሱን የሚ​ፈ​ራና እው​ነ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ በእ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነው።


ጴጥ​ሮ​ስም ሕዝ​ቡን ባያ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ለምን ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ? እኛ​ንስ በኀ​ይ​ላ​ች​ንና በጽ​ድ​ቃ​ችን ይህን ሰው በእ​ግሩ እን​ዲ​ሄድ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ነው አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ለምን ታዩ​ና​ላ​ችሁ?


“እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እን​ደ​ም​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ባደ​ረ​ገው በከ​ሃ​ሊ​ነቱ በተ​አ​ም​ራ​ቱና በድ​ንቅ ሥራ​ዎቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ለ​ጠ​ላ​ች​ሁን ሰው የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን ስሙ።


ጴጥ​ሮ​ስም ከዐ​ሥራ አንዱ ጋር ቆሞ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “እና​ንተ የአ​ይ​ሁድ ሰዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የም​ት​ኖሩ ሁሉ፥ ይህን ዕወቁ፤ ቃሌ​ንም ስሙ።


ይቅ​ር​ታ​ውም ለሚ​ፈ​ሩት ለልጅ ልጅ ነው።


የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።


የባ​ሳ​ንን ንጉሥ ዐግን፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ ይምጡ፥ አቤቱ፥ በፊ​ት​ህም ይስ​ገዱ፥ ስም​ህ​ንም ያክ​ብሩ፤


አቤቱ፥ በሕ​ዝ​ብህ ፊት በወ​ጣህ ጊዜ፥ በም​ድረ በዳም ባለ​ፍህ ጊዜ፥


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በሰ​ጠ​ሃት ምድር ላይ በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ይፈ​ሩህ ዘንድ።


ጓደ​ኛ​ውም መልሶ ገሠ​ጸው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አንተ በዚህ ፍርድ ውስጥ ሳለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን አት​ፈ​ራ​ው​ምን?


ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜም እነ​ር​ሱን ማነ​ጋ​ገር ተሳ​ነው፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም የተ​ገ​ለ​ጠ​ለት እን​ዳለ ዐወቁ፤ እን​ዲ​ሁም ዲዳ ሆኖ በእጁ እያ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸው ኖረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios