Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 15:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እነ​ር​ሱም ጸጥ ባሉ ጊዜ ያዕ​ቆብ መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስሙኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እነርሱም ተናግረው ሲጨርሱ፣ ያዕቆብ ተነሥቶ በመቆም እንዲህ አለ፤ “ወንድሞች ሆይ፤ ስሙኝ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነርሱም ዝም ካሉ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰ “ወንድሞች ሆይ! ስሙኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እነርሱ ተናግረው ካበቁ በኋላ፥ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ወንድሞች ሆይ! እስቲ ስሙኝ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እነርሱም ዝም ካሉ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “ወንድሞች ሆይ፥ ስሙኝ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 15:13
15 Referencias Cruzadas  

ሴቶችም ደግሞ በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜም ነበሩ፤


እርሱ ግን ዝም እን​ዲሉ በእጁ አመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፤ ከወ​ኅኒ ቤትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ጣው ነገ​ራ​ቸው፤ “ይህ​ንም ለያ​ዕ​ቆ​ብና ለወ​ን​ድ​ሞች ሁሉ ንገሩ” አላ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።


ስም​ዖ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ አሕ​ዛ​ብን ይቅር እን​ዳ​ላ​ቸ​ውና ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ለስሙ ሕዝ​ብን እንደ መረጠ ተና​ግ​ሮ​አል።


ጴጥ​ሮ​ስም ከዐ​ሥራ አንዱ ጋር ቆሞ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “እና​ንተ የአ​ይ​ሁድ ሰዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የም​ት​ኖሩ ሁሉ፥ ይህን ዕወቁ፤ ቃሌ​ንም ስሙ።


“እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እን​ደ​ም​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ባደ​ረ​ገው በከ​ሃ​ሊ​ነቱ በተ​አ​ም​ራ​ቱና በድ​ንቅ ሥራ​ዎቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ለ​ጠ​ላ​ች​ሁን ሰው የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን ስሙ።


“እና​ንተ ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስለ አባ​ቶች አለቃ ስለ ዳዊት ነገር እንደ ሞተ እንደ ተቀ​በ​ረም፥ መቃ​ብ​ሩም እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ እንደ አለ ገልጬ እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ትፈ​ቅ​ዱ​ል​ኛ​ላ​ች​ሁን?


በማ​ግ​ሥ​ቱም ጳው​ሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕ​ቆብ ገባ፤ ቀሳ​ው​ስ​ትም ሁሉ በዚያ ነበሩ።


“እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ችና አባ​ቶች፥ አሁን በፊ​ታ​ችሁ የም​ና​ገ​ረ​ውን ስሙኝ።”


እር​ሱም እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንና አባ​ቶ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስሙ፤ የክ​ብር አም​ላክ ለአ​ባ​ታ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃም በሁ​ለት ወን​ዞች መካ​ከል ሳለ ወደ ካራ​ንም ሳይ​መጣ ተገ​ለ​ጠ​ለት።


ነገር ግን የጌ​ታ​ችን ወን​ድም ያዕ​ቆ​ብን እንጂ ከሐ​ዋ​ር​ያት ሌላ አላ​የ​ሁም።


ሰዎች ከያ​ዕ​ቆብ ዘንድ ከመ​ም​ጣ​ታ​ቸው በፊት፥ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ጋር ይበላ ነበ​ርና፥ በመጡ ጊዜ ግን ተለ​ያ​ቸው፤ ከአ​ይ​ሁድ ወገን የሆ​ኑ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና።


የሰ​ጠ​ኝ​ንም ጸጋ ዐው​ቀው አዕ​ማድ የሚ​ሏ​ቸው ያዕ​ቆ​ብና ኬፋ፥ ዮሐ​ን​ስም እኛ ወደ አሕ​ዛብ፥ እነ​ር​ሱም ወደ አይ​ሁድ እን​ድ​ን​ሄድ ለእ​ኔና ለበ​ር​ና​ባስ ቀኝ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።


የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos