ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እንዲህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ በፊትህ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ፤ እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ፤ አንተ ከፈርዖን ቀጥለህ ነህና።
1 ሳሙኤል 26:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእኔን የአገልጋይህን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አስነሥቶህ እንደሆነ፥ ቍርባንህን ይቀበል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ላይ እንዳልቀመጥ ዛሬ ጥለውኛልና በእግዚአብሔር ፊት ርጉማን ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባሪያውን ቃል ያድምጥ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደ ሆነ፣ ቍርባን ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፣ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ፤ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳድደውኛልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባርያውን ቃል ያድምጥ፤ ጌታ በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደሆነ፥ መሥዋዕት ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፥ በጌታ ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በጌታ ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳደውኛልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሆይ! የምልህን አድምጠኝ! አንተን በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፥ መሥዋዕት በማቅረብ ቊጣውን እንዲመልስ ማድረግ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ ሄደህ ባዕዳን አማልክትን አምልክ ብለው እግዚአብሔር ከሰጠኝ ርስት ድርሻ ስላባረሩኝ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የእኔን የባሪያህን ቃል ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ፥ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አስነሥቶህ እንደ ሆነ፥ ቁርባንን ይቀበል፥ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ላይ እንዳልቀመጥ ዛሬ ጥለውኛልና በእግዚአብሔር ፊት ርጉማን ይሁኑ። |
ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እንዲህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ በፊትህ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ፤ እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ፤ አንተ ከፈርዖን ቀጥለህ ነህና።
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
ንጉሡም፥ “እናንተ የሶርህያ ልጆች! በእኔና በእናንተ መካከል ምን አለኝ? እግዚአብሔር ዳዊትን ርገመው ብሎ አዝዞታልና ይርገመኝ፤ ለምንስ እንዲህ ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?” አለ።
ዳዊትም አቢሳንና አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “እነሆ፥ ከወገቤ የወጣው ልጄ ነፍሴን ይሻል፤ ይልቁንስ ይህ የኢያሚን ልጅ እንዴት ነዋ? እግዚአብሔር አዝዞታልና ተዉት፥ ይርገመኝ።
በእስራኤል ኀያላን ዘንድ ሰላምን ከሚወድዱት አንድዋ ነኝ፤ አንተ ግን በእስራኤል ያለችውን ከተማና እናት ከተማን ለማፍረስ ትሻለህ፤ ስለምንስ የእግዚአብሔርን ርስት ታጠፋለህ?”
ዳዊትም የገባዖንን ሰዎች፥ “የእግዚአብሔርን ርስት ትባርኩ ዘንድ ምን ላድርግላችሁ? ማስተስረያውስ ምንድን ነው?” አላቸው።
ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊትንም፥ “ሂድ፤ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር” ብሎ በላያቸው አስነሣው።
እግዚአብሔርም፦ በምን ታስተዋለህ? አለው፤ እርሱም ወጥቼ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፤ ይሆንልሃልም፤ ውጣ፤ እንዲሁም አድርግ አለ።
ከተሞቻችሁንም ባድማ አደርጋለሁ፤ መቅደሶቻችሁንም አፈርሳለሁ፤ የመሥዋዕታችሁንም መዓዛ አላሸትትም።
እንደዚህም የእስራኤል ልጆች ርስት ከነገድ ወደ ነገድ ምንም አይተላለፍ፤ ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ወደ አባቶቹ ነገድ ርስት ይጠጋ።
እንደዚህም ከአንድ ነገድ ወደ ሌላ ነገድ ምንም ርስት አይተላለፍ። ከእስራኤልም ልጆች ነገድ እያንዳንዱ ወደ ርስቱ ይጠጋ።”
በመብል ምክንያት ባልንጀራህን የምታሳዝን ከሆንህ ፍቅር የለህም፤ በውኑ ክርስቶስ ስለ እርሱ የሞተለት ያ ሰው በመብል ምክንያት ሊጐዳ ይገባልን?
አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደሆን ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ ነውና የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስሙ።
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሳኦልን ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው፤ በቤቱም ውስጥ ትንቢት ተናገረ። ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ እንደ ነበረ በእጁ በገና ይመታ ነበር። ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።
ከእርሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፤ ከዋሻውም ወጣ፤ ከሳኦልም በኋላ፦“ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጮኸ፤ ሳኦልም ወደ ኋላው ተመለከተ፤ ዳዊትም ወደ ምድር ተጐንብሶ እጅ ነሣ።
በእግሩም ላይ ወደቀች፤ እንዲህም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ኀጢኣት በእኔ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪያህ በጆሮህ ልናገር፥ የባሪያህንም ቃል አድምጥ።
ዳዊትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሸ በቀር የሚሻለኝ የለም፤ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፤ እንዲሁም ከእጁ እድናለሁ” አለ።