Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 25:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በእ​ግ​ሩም ላይ ወደ​ቀች፤ እን​ዲ​ህም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ይህ ኀጢ​ኣት በእኔ ላይ ይሁን፤ እኔ ባሪ​ያህ በጆ​ሮህ ልና​ገር፥ የባ​ሪ​ያ​ህ​ንም ቃል አድ​ምጥ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በእግሩም ላይ ወድቃ እንዲህ አለች፤ “ጌታዬ ሆይ፤ በደሉ በእኔ ላይ ብቻ ይሁን፤ እባክህ አገልጋይህ ታናግርህ፤ የምትልህንም ስማ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በእግሩም ላይ ወድቃ እንዲህ አለች፤ “ጌታዬ ሆይ፤ በደሉ በእኔ ላይ ብቻ ይሁን፤ እባክህ አገልጋይህ ታናግርህ፤ የምትልህንም ስማ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በጫማውም ላይ ወድቃ እንዲህ አለች፦ “ጌታዬ ሆይ! እባክህ የእኔን የአገልጋይህን ቃል አድምጠኝ! በደሉን እኔ ልሸከም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በእግሩም ላይ ወደቀች፥ እንዲህም አለች፦ ጌታዬ ሆይ፥ ይህ ኃጢአት በእኔ ላይ ይሁን፥ እኔ ባሪያህ በጆሮህ ልናገር፥ የባሪያህንም ቃል አድምጥ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 25:24
15 Referencias Cruzadas  

ይሁ​ዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በፊ​ትህ አን​ዲት ቃልን እን​ድ​ና​ገር እለ​ም​ና​ለሁ፤ እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አት​ቈ​ጣኝ፤ አንተ ከፈ​ር​ዖን ቀጥ​ለህ ነህና።


ሴቲ​ቱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ አንድ ቃል ልና​ገር” አለች፤ እር​ሱም፥ “ተና​ገሪ” አላት።


የቴ​ቁ​ሔ​ዪ​ቱም ሴት ንጉ​ሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ኀጢ​አቱ በእ​ኔና በአ​ባቴ ቤት ላይ ይሁን፤ ንጉ​ሡና ዙፋኑ ንጹሕ ይሁን” አለ​ችው።


ሴቲ​ቱም፥ “ኢዮ​አብ አንተ ነህን?” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እኔ ነኝ” ብሎ መለ​ሰ​ላት። እር​ስ​ዋም፥ “የባ​ሪ​ያ​ህን ቃል ስማ” አለ​ችው። ኢዮ​አ​ብም፥ “እሰ​ማ​ለሁ” አላት።


ሴት​ዮ​ዋም ገብታ በእ​ግሩ አጠ​ገብ ወደ​ቀች በም​ድ​ርም ላይ ሰገ​ደች፤ ልጅ​ዋ​ንም አን​ሥታ ወጣች።


ትዕ​ግ​ሥት ታላ​ቁን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ልና የገዢ ቍጣ የተ​ነ​ሣ​ብህ እንደ ሆነ ስፍ​ራ​ህን አት​ል​ቀቅ።


ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ ‘ታገሠኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፤’ ብሎ ለመነው።


ዳዊ​ትም በዚህ ቃል ሰዎ​ቹን ከለ​ከ​ላ​ቸው። በሳ​ኦ​ልም ላይ ተነ​ሥ​ተው ይገድ​ሉት ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸ​ውም፤ ሳኦ​ልም ከዋ​ሻው ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ።


አቤ​ግ​ያም ዳዊ​ትን ባየች ጊዜ ከአ​ህ​ያዋ ላይ ፈጥና ወረ​ደች፤ በዳ​ዊ​ትም ፊት በግ​ን​ባ​ርዋ ወደ​ቀች፤ ምድ​ርም ነክታ ሰገ​ደ​ች​ለት።


በዚህ ክፉ ሰው በና​ባል ላይ ጌታዬ ልቡን እን​ዳ​ይ​ጥል እለ​ም​ና​ለሁ፤ እንደ ስሙ እን​ዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስን​ፍ​ናም አድ​ሮ​በ​ታል፤ እኔ ባሪ​ያህ ግን አንተ የላ​ክ​ሃ​ቸ​ውን ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህን አላ​የ​ሁም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ የታ​መነ ቤትን ይሠ​ራ​ለ​ታ​ልና፥ የጌ​ታ​ዬ​ንም ጦር​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይዋ​ጋ​ለ​ታ​ልና የእ​ኔን የባ​ሪ​ያ​ህን ኀጢ​ኣት፥ እባ​ክህ፥ ይቅር በል፤ በዘ​መ​ን​ህም ሁሉ ክፋት አይ​ገ​ኝ​ብ​ህም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos