Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ያን​ጊ​ዜም ሰይ​ጣን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ይቈ​ጥር ዘንድ ዳዊ​ትን አነ​ሣ​ሣው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሰይጣን በእስራኤል ላይ ተነሥቶ ዳዊት የእስራኤልን ሕዝብ እንዲቈጥር አነሣሣው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም እንዲቈጥር ዳዊትን አነሣሣው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ሰይጣን በእስራኤል ሕዝብ ላይ ተነሥቶ ዳዊትን የሕዝብ ቈጠራ እንዲያደርግ አነሣሣው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፤ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን አነሣሣው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 21:1
18 Referencias Cruzadas  

እነ​ዚ​ህም በጌት ውስጥ ከኀ​ያ​ላን የተ​ወ​ለዱ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም አራት ኀያ​ላን ነበሩ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ ወደቁ።


የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብም መቍ​ጠር ጀመረ፤ ነገር ግን አል​ፈ​ጸ​መም፤ ስለ​ዚህ ነገር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቍጣ ሆነ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በን​ጉሡ በዳ​ዊት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ አል​ተ​ጻ​ፈም።


እነ​ዚህ ሁሉ የአ​ሴር ልጆች፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ የተ​መ​ረጡ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች፥ የመ​ኳ​ን​ንቱ አለ​ቆች ነበሩ። በት​ው​ል​ዳ​ቸ​ውም በሰ​ልፍ ለመ​ዋ​ጋት የተ​ቈ​ጠሩ ሃያ ስድ​ስት ሺህ ሰዎች ነበሩ።


ከዕ​ለ​ታት አንድ ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት መጥ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሙ፥ ሰይ​ጣን ደግሞ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ቆም ከእ​ነ​ርሱ ጋር መጣ።


“አንተ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቍጥር የወ​ሰ​ድህ እንደ ሆነ በቈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ጊዜ መቅ​ሠ​ፍት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ በቈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን የነ​ፍ​ሱን ቤዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይስጥ።


እርሱም ታላቁን ካህን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንም ይከስሰው ዘንድ በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር።


ፈታኝም ቀርቦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል!” አለው።


በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት ይህን ሲነ​ግ​ራ​ቸው ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን አጽ​ን​ተው ይጣ​ሉት፥ ይቀ​የ​ሙ​ትም ጀመር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ስም​ዖን፥ ስም​ዖን ሆይ፥ ሰይ​ጣን እንደ አጃ ሊያ​በ​ጥ​ራ​ችሁ አሁን ልመ​ናን ለመነ።


ራት ሲበ​ሉም አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ በስ​ም​ዖን ልጅ በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ።


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ሐና​ንያ ሆይ፥ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ታታ​ል​ለው ዘንድ፥ የመ​ሬ​ት​ህ​ንም ዋጋ ከፍ​ለህ ታስ​ቀር ዘንድ ሰይ​ጣን በል​ብህ እን​ዴት አደረ?


በፍ​ቅ​ርና በበጎ ምግ​ባ​ርም ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችን ጋር እን​ፎ​ካ​ከር።


ማንም ሲፈተን “በእግዚአብሔር እፈተናለሁ፤” አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።


ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳንና ኀይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸውየወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos