Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነ​ዚ​ህም በጌት ውስጥ ከኀ​ያ​ላን የተ​ወ​ለዱ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም አራት ኀያ​ላን ነበሩ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ ወደቁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በጋት የነበሩ የራፋይም ዘሮች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም በዳዊትና በሰዎቹ እጅ ወደቁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነዚያም በጌት ውስጥ ከራፋይም የተወለዱ ነበሩ፤ በዳዊትም እጅ በባርያዎቹም እጅ ወደቁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በዳዊትና በሠራዊቱ የተገደሉት እነዚህ ሦስቱ ሰዎች ኀያላን ከሆኑት የራፋይም ዘር ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እነዚያም በጌት ውስጥ ከራፋይም የተወለዱ ነበሩ፤ በዳዊትና በባሪያዎቹ እጅ ወደቁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 20:8
8 Referencias Cruzadas  

ከራ​ፋ​ይም ወገን የነ​በ​ረው ኤስቢ መጣ፤ የጦ​ሩም ሚዛን ክብ​ደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣ​ሪ​ያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊ​ት​ንም ሊገ​ድ​ለው ፈለገ።


እነ​ዚ​ያም አራቱ በጌት ውስጥ ከረ​ዐ​ይት የተ​ወ​ለዱ የራ​ፋ​ይም ወገ​ኖች ነበሩ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ ወደቁ።


እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ገ​ዳ​ደረ ጊዜ የዳ​ዊት ወን​ድም የሳ​ምዓ ልጅ ዮና​ታን ገደ​ለው።


ያን​ጊ​ዜም ሰይ​ጣን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተነሣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ይቈ​ጥር ዘንድ ዳዊ​ትን አነ​ሣ​ሣው።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ሩጫ ለፈ​ጣ​ኖች፥ ጦር​ነ​ትም ለኀ​ያ​ላን፥ እን​ጀ​ራም ለጠ​ቢ​ባን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች፥ ሞገ​ስም ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ዳ​ል​ሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገ​ና​ኛ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ባለ​ጠ​ጋም በብ​ል​ጥ​ግ​ናው አይ​መካ፤


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


አሁን እን​ግ​ዲህ በዚያ ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ይህን ተራ​ራማ ሀገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔና​ቃ​ው​ያን፥ ታላ​ላ​ቆ​ችና የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችም በዚያ እን​ዳሉ ሰም​ተህ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ረኝ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos