መዝሙር 134:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ አገልጋዮቹ! በሌሊት በመቅደሱ የምታገለግሉት ሁሉ፥ ኑ እግዚአብሔርን አመስግኑ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በሌሊት ቆማችሁ በእግዚአብሔር ቤት የምታገለግሉ፣ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ እግዚአብሔርን ባርኩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዕርገት መዝሙር። እነሆ፥ ጌታን ባርኩ፥ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የጌታ ባርያዎች ሁላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ፤ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት። |
ሌሎች የሌዋውያን ቤተሰቦች አለቆች መዘምራን ነበሩ፤ እነርሱ ሌት ተቀን የማገልገል ኀላፊነት ስለ ነበረባቸው ከሌሎች አገልግሎቶች ነጻ በመሆን በቤተ መቅደሱ ቅጽር ግቢ በተዘጋጁላቸው ክፍሎች ውስጥ ይኖሩ ነበር።
ልጆቼ ሆይ! በፊቱ ቆማችሁ እንድታገለግሉትና የእርሱ አገልጋዮች እንድትሆኑ፥ መሥዋዕትንም እንድታቀርቡ እግዚአብሔር የመረጣችሁ ስለ ሆነ እንግዲህ ቸልተኞች አትሁኑ።”
እናንተ ሌዋውያን፥ እያንዳንዱን የእስራኤል ሕዝብ ቤተሰብ ለመርዳት እንድትችሉ እየተከፋፈላችሁ በተቀደሰው ስፍራ በቦታ በቦታቸው ራሳችሁን አደራጁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዐይኖቼም ትዕቢተኞች አይደሉም፤ ስለ ታላላቅ ነገሮች ወይም ላስተውለው ስለማልችለው ከባድ ነገር አልጨነቅም።
ስለዚህም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ በመፈጸም ሰባት ቀን ሙሉ ሌሊትና ቀን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ትቈያላችሁ፤ ይህን ባታደርጉ ግን ትሞታላችሁ፤ ይህ እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሕግ ነው።”
ከዚህም በኋላ ዕድሜዋ ሰማኒያ አራት ዓመት እስኪሆን ድረስ ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በጾምና በጸሎት ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ታገለግል ነበር።
በዚያን ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከሙ፥ በፊቱም በመቆም እንዲያገለግሉትና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ የሌዊን ነገድ በመለየት ሾመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሌዊ ነገድ ትውልድ አገልግሎት ይኸው ነው።