Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 113 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


የእግዚአብሔርን ቸርነት የሚገልጥ ምስጋና

1 እግዚአብሔር ይመስገን! እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ!

2 አሁንም ለዘለዓለም ስሙ ይመስገን።

3 ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!

4 እግዚአብሔር የመንግሥታት ሁሉ ገዢ ነው፤ ክብሩም ከሰማያት ሁሉ በላይ ነው።

5 እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም፤ ዙፋኑም ከሁሉ በላይ ነው።

6 ነገር ግን ሰማይንና ምድርን ወደ ታች ይመለከታል።

7 ድኾችን ከትቢያ ችግረኞችንም ከዐመድ ቊልል ያነሣቸዋል።

8 የልዑላን ጓደኞች ያደርጋቸዋል፤ ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያስቀምጣቸዋል።

9 መኻኒቱንም በቤቷ በክብር ያኖራታል፤ ልጆችንም በመስጠት ደስ ያሰኛታል። እግዚአብሔር ይመስገን!

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos