1 እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዐይኖቼም ትዕቢተኞች አይደሉም፤ ስለ ታላላቅ ነገሮች ወይም ላስተውለው ስለማልችለው ከባድ ነገር አልጨነቅም።
2 አንድ ጡት የተወ ሕፃን በእናቱ ደረት ላይ እንደሚለጠፍ እኔም ዝምተኛና ጸጥተኛ ሆንኩ።
3 እስራኤል ሆይ! ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ!
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997