መዝሙር 127 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምስለ እግዚአብሔር ቸርነት የቀረበ ምስጋና 1 እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ የቤት ሠሪዎች ድካም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ የከተማ ጠባቂዎች ትጋት ከንቱ ነው። 2 በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ገና ተኝተው ሳሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል። 3 ልጆች ከእግዚአብሔር የሚገኙ ስጦታዎች ናቸው፤ እውነተኛም በረከት ናቸው። 4 ሰው በወጣትነቱ የሚወልዳቸው ወንዶች ልጆች በወታደር እጅ እንዳሉ ፍላጻዎች ናቸው። 5 እንደነዚህ ፍላጻዎች የሆኑ ብዙ ልጆች ያሉት ሰው የታደለ ነው፤ ከጠላቶቹ ጋር በፍርድ አደባባይ በሚከራከርበት ጊዜ ከቶ አይሸነፍም። |