Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 129 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


ከእስራኤል ጠላቶች ለመዳን የቀረበ መዝሙር

1 ከወጣትነቴ ጀምሮ አደጋ ደርሶብኛል፤ እስራኤላውያን እንዲህ ይበሉ፦

2 “ከወጣትነቴ ጀምሮ ጠላቶቼ በጭካኔ አሳደዱኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም።

3 ጀርባዬን በጅራፍ ተልትለው፥ የታረሰ ማሳ አስመስለውታል።

4 እግዚአብሔር ሁልጊዜ ትክክለኛ ነው፤ ከእነዚያ ጨካኞች ገመድ ነጻ አውጥቶኛል።”

5 ጽዮንን የሚጠላ ሁሉ ይሸነፍ! ወደ ኋላውም ይመለስ!

6 በቤት ጣራ ላይ እንደሚበቅልና ከማደጉ በፊት እንደሚደርቅ ሣር ይሁን።

7 እንዲህ ዐይነቱን ሣር ማንም አይሰበስበውም፤ ወይም ነዶው በእጁ አይሞላም።

8 በአጠገባቸው የሚያልፉት ሁሉ ለጽዮን ጠላቶች “እግዚአብሔር ይባርካችሁ! እኛም በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን!” አይሉአቸውም።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos