አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ።
ኤርምያስ 25:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የዓሞን ልጅ ኢዮስያስ በይሁዳ ከነገሠ ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እግዚአብሔር እስከ ዛሬ ድረስ ለኻያ ሦስት ዓመት ሲናገረኝ ቈይቶአል፤ የእርሱንም ቃል ለእናንተ ከመናገር ከቶ አልቦዘንኩም፤ እናንተ ግን ልብ ብላችሁ አላስተዋላችሁም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ንጉሥ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ ከነገሠበት ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሃያ ሦስት ዓመት ሙሉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ ደጋግሜም ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት፥ የጌታ ቃል ወደ እኔ መጣ፥ እኔም ማልጄ ተነሥቼ ተናገርኋችሁ፤ ተናገርሁ፥ ሆኖም ግን አልሰማችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ ከዐሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሃያ ሦስቱ ዓመታት፥ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ማልጄ ተነሥቼ ተናገርኋችሁ፤ ነገር ግን አልሰማችሁኝም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ ከአሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት፥ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፥ እኔም ማልጄ ተነሥቼ ተናገርኋችሁ፥ ነገር ግን አልሰማችሁም። |
አብርሃም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ለመሥዋዕቱ የሚሆን እንጨት ቈረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅንና ሁለት አገልጋዮችን ይዞ እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ ለመሄድ ጒዞ ጀመረ።
አክዓብ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖች “በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትን ከሶርያ ንጉሥ ለማስመለስ ምንም ዐይነት እርምጃ ያልወሰድነው ስለምንድን ነው? ራሞት እኮ የእኛ ይዞታ ናት!” አላቸው፤
እግዚአብሔርም እስራኤልንና ይሁዳን የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞችንና ነቢያትን በመላክ “ከክፉ መንገዳችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ አገልጋዮቼ በሆኑት ነቢያትና ባለ ራእዮች አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተም በሰጠሁት ሕጎችና ትእዛዞች የተጻፈውን ሥርዓቴን ጠብቁ” ብሎ ነግሮአቸው ነበር።
ኢዮስያስ በነገሠ በስምንተኛ ዓመቱ፥ ገና ወጣት ሳለ የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን አምላክ እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመረ፤ ከአራት ዓመት በኋላም የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎችን፥ አሼራ ተብላ የምትጠራ የሴት አምላክ ምስሎችንና ሌሎችን ጣዖቶች ሁሉ ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ማስወገድ ጀመረ፤
ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የአሕዛብን አምልኮ በማጥፋት ምድሪቱንና ቤተ መቅደሱን ካነጻ በኋላ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ያድሱ ዘንድ የአጻልያን ልጅ ሳፋንን፥ የኢየሩሳሌም አስተዳዳሪ የሆነውን ማዕሤያንና የኢዮአሐዝን ልጅ ጸሐፊውን ዮአሕን ላከ፤
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ነገ ጠዋት በማለዳ ወደ ንጉሡ ሄደህ ወደ ወንዝ ሲወርድ አግኘው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤
ለማይጠቅም ምግብ ገንዘባችሁን ለምን ታወጣላችሁ? ለማያጠግብ ነገር ጒልበታችሁን ለምን ታባክናላችሁ? አሁንም በጥንቃቄ አድምጡኝና መልካም የሆነውን ምግብ ብሉ፤ በምርጥ ምግብም ራሳችሁን አስደስቱ።
የቀድሞ አባቶቻቸውን ከግብጽ ባወጣኋቸው ጊዜ ለእኔ እንዲታዘዙ ደጋግሜ አስጠነቀቅኋቸው፤ ሕዝቡንም እስከ ዛሬው ቀን ድረስ እንኳ ከማስጠንቀቅ አልተቈጠብኩም።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነርሱ እልኸኞች ሆነው ለቃሌ ስላልታዘዙ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ በሚገኙ ስፍራዎች ሁሉ ይመጣል ብዬ ያስታወቅኹትን መቅሠፍት ሁሉ አመጣባቸዋለሁ።”
በብልጽግና በምትኖሩበት ጊዜ እግዚአብሔር ተናገራችሁ፤ እናንተ ግን ማዳመጥ እምቢ አላችሁ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ የምታደርጉት ይህንኑ ነው። እግዚአብሔርንም መታዘዝ እምቢ አላችሁ።
የኢዮናዳብ ዘሮች እንኳ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ አባታቸው ያዘዛቸውን ቃል በመጠበቅ እነሆ እስከ አሁን ድረስ ምንም ዐይነት የወይን ጠጅ አይቀምሱም፤ እኔ ግን ሁልጊዜ በመደጋገም እነግራችኋለሁ፤ እናንተ ልትታዘዙኝ አልፈለጋችሁም፤
አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያትን ወደ እናንተ ደጋግሜ ልኬአለሁ፤ እነርሱም ከክፉ ሥራችሁ ተመልሳችሁ ቅን የሆነውን ነገር እንድትሠሩ ነግረዋችኋል፤ ለባዕዳን አማልክት እንዳትሰግዱና የእነርሱም አገልጋዮች እንዳትሆኑ አስጠንቅቀዋችኋል፤ ለእናንተና ለቀድሞ አባቶቻችሁ በሰጠኋችሁ ምድር መኖር ትችሉ ዘንድ ይህን ሁሉ አዘዝኳችሁ፤ እናንተ ግን እኔን ለማዳመጥም ሆነ ለምነግራችሁ ቃል ትኲረት ልትሰጡት አልፈለጋችሁም።
“እኔ እግዚአብሔር አንተን ማናገር ከጀመርኩበት ማለትም ኢዮስያስ ከነገሠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስለ እስራኤል፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብና ስለ ሌሎችም ሕዝቦች ሁሉ የነገርኩህን ቃል ሁሉ በብራና ጻፈው፤
የቀድሞ አባቶቻችሁ ከግብጽ ከወጡበት ቀን አንሥቶ እስከዚህች ቀን ድረስ አገልጋዮቼን ነቢያትን እያከታተልኩ ከመላክ የተቈጠብኩበት ጊዜ የለም።
እንደ ቀድሞ አባቶቻችሁ አትሁኑ፤ እነርሱን የቀድሞ ነቢያት ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ’ ብለው አስጠንቅቀዋቸው ነበር፤ አባቶቻችሁ ግን ቃሌን አላደመጡም፤ ትእዛዜንም አልጠበቁም።