Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 55:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ለማይጠቅም ምግብ ገንዘባችሁን ለምን ታወጣላችሁ? ለማያጠግብ ነገር ጒልበታችሁን ለምን ታባክናላችሁ? አሁንም በጥንቃቄ አድምጡኝና መልካም የሆነውን ምግብ ብሉ፤ በምርጥ ምግብም ራሳችሁን አስደስቱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ? በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጕልበታችሁን ትጨርሳላችሁ? ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ገን​ዘ​ብን እን​ጀራ ላይ​ደለ፥ የድ​ካ​ማ​ች​ሁ​ንም ዋጋ ለማ​ያ​ጠ​ግብ ነገር ለምን ትመ​ዝ​ና​ላ​ችሁ? አድ​ም​ጡኝ፤ በረ​ከ​ት​ንም ብሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ደስ ይበ​ለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 55:2
42 Referencias Cruzadas  

ድኾች እስኪጠግቡ ይበላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይደሰታል።


ልጆቼ ሆይ! ኑ አድምጡኝ፤ እኔም እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።


በቤትህ የተትረፈረፈውን ምግብ ይጋበዛሉ፤ አስደሳች ከሆነ ወንዝህም ታጠጣቸዋለህ።


ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር በደስታ እዘምርልሃለሁ።


እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


እኔን የሚሰማ ግን ለሕይወቱ ዋስትና ይኖረዋል፤ ምንም የሚያስፈራው ነገር ሳይደርስበት በሰላም ይኖራል።”


ፍላጻም ሆድ ዕቃውን እንደሚወጋው ዐይነት ሆነ፤ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ ወፍ መሰለ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕይወቱ በአደጋ ላይ ለመውደቅ መቃረቡን አላወቀም።


“ልጆቼ ሆይ! አድምጡኝ መንገዴን የሚከተሉ ይደሰታሉ።


“ና ያዘጋጀሁትን ምግብ ብላ! የጠመቅኩትንም የወይን ጠጅ ጠጣ!


እግዚአብሔር ለሰው ምድራዊ ሀብትንና ብልጽግናን ክብርንም ሁሉ ይሰጠዋል፤ ከሚያስፈልገውም ነገር ሁሉ ምንም አያጐድልበትም፤ ይሁን እንጂ በሚሰጠው ሀብት ሁሉ አይደሰትበትም፤ ይልቁንም እርሱ ደክሞ ያፈራውን ሌላ ሰው ይደሰትበታል። ይህም ከንቱና እጅግ የከፋ በደል ነው።


እሺ ብላችሁ ብትታዘዙኝ ምድር የምታስገኘውን በረከት ትበላላችሁ፤


በዚያንም ጊዜ እናንተን ከአሦራውያን የጭቈና አገዛዝ ነጻ አወጣችኋለሁ፤ ከዚያን በኋላ የአገዛዝ ቀንበራቸው ከውፍረታችሁ የተነሣ ይሰበራል እንጂ በእናንተ ጫንቃ ላይ እንደተጫነ አይቀርም።”


የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።


ተቃጥሎ ዐመድ የሚሆነውን እንጨት እስከ ማምለክ ድረስ ሰው እንዴት ሞኝ ይሆናል? የሞኝነት አስተሳሰቡ አሳስቶታል፤ ራሱን ማዳን አይችልም፤ ወይም “ይህ በቀኝ እጄ ያለው ነገር ጣዖት እንጂ አምላክ አይደለም።” ብሎ መናገር አይችልም።


አንዳንድ ሰዎች ኰረጆአቸውን ከፍተው ወርቅ እንደ ልባቸው ይመዛሉ፤ ብሩንም በሚዛን ይመዝናሉ፤ ጣዖት አድርጎ እንዲሠራላቸውም አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ ከተሠራም በኋላ እየሰገዱ ያመልኩታል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔንና ጽድቅን የምትፈልጉ አድምጡኝ፤ ወደ ተጠረባችሁበት ድንጋይና ወደ ወጣችሁበት ጒድጓድ ተመልከቱ።


“ሕዝቤ ሆይ! ስሙ! የምላችሁንም አድምጡ ሕግ ከእኔ ይገኛል፤ ፍርዴም ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን ይሆናል።


“እናንተ ትክክለኛውን ነገር የምታውቁና ሕጌ በልባችሁ ያለ ሰዎች አድምጡኝ፤ የሰዎችን ነቀፋ አትፍሩ፤ ወይም በስድባቸው አትደናገጡ።


እግዚአብሔር በኃይሉና በሥልጣኑ እንዲህ ሲል ማለ፦ “ከእንግዲህ ወዲያ እህልሽን ጠላቶችሽ እንዲበሉት አላደርግም፤ የደከምሽበትን አዲስ የወይን ጠጅሽንም ባዕዳን እንዲጠጡት አላደርግም።


ነገር ግን በጐተራ የሰበሰቡትን እህል እነርሱ ራሳቸው በልተው እኔ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፤ የሰበሰቡትንም የወይን ዘለላ የወይን ጠጅ እነርሱ ራሳቸው በተቀደሰ አደባባዬ ይጠጡታል።


ሥራቸው ከንቱ አይሆንም፤ የወለዱአቸው ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው በእግዚአብሔር የተባረኩ ስለሚሆኑ ልጆቹን የሚወልዱት ጥፋት እንዲደርስባቸው አይደለም።


ሕዝቤ ስንዴ ዘርተው እሾኽ ሰበሰቡ፤ በሥራ እጅግ ደክመው ምንም ትርፍ አላገኙም፤ ከብርቱ ቊጣዬ የተነሣ በምርታቸው መጥፋት አዘኑ።”


“‘እንግዲህ የሚያዳምጡኝ ከሆኑ እነዚህ ሕዝብ ትእዛዜን እንዲጠብቁ ንገራቸው፤ በሰንበት ቀን ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው በከተማይቱ በሮች አይግቡ፤ ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርገው ያክብሩ እንጂ በዚያን ቀን ምንም ሥራ አይሥሩ።


ሕዝቤ ሁለት ኃጢአት ሠርተዋል፤ ይኸውም የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆንኩትን እኔን ትተውኛል፤ ውሃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጒድጓዶችን ለራሳቸው ቆፍረዋል።”


ካህናቱን በምድሪቱ በረከት አጠግባቸዋለሁ፤ ለሕዝቤም ቸርነቴን አትረፈርፍላቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


“የእስራኤል ሕዝብ ነፋስን ለመጨበጥ በመሞከርና ቀኑን ሙሉ የምሥራቅ ነፋስን ሲያሳድዱ በመዋል ከንቱ ሆነዋል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛሉ፤ ከአሦር ጋር ይዋዋላሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የወይራ ዘይትን ወደ ግብጽ ይልካሉ።”


እነርሱ ነፋስን ዘርቶ ዐውሎ ነፋስን እንደሚያጭድ ይሆናሉ፤ ዛላ የሌለው የእህል አገዳ ምግብ ሊሆን አይችልም፤ ፍሬ ቢኖረውም እንኳ የሚበሉት ባዕዳን በሆኑ ነበር።


ሰዎች የሚሠሩት ለቃጠሎ፥ መንግሥታትም የሚደክሙት ምንም ጥቅም ለሌለው ነገር እንዲሆን የሚያደርግ የሠራዊት አምላክ አይደለምን?


ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን፥ እንደ ሕግ አድርጎ እያስተማረ በከንቱ ያመልከኛል።’ ”


“ንጉሡ ሌሎች አገልጋዮችን እንደገና እንዲህ ሲል ላከ፤ ‘ወደ ተጠሩት ሰዎች ሂዱና፦ እነሆ፥ የሠርግ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ፍሪዳዎቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶአል፤ ስለዚህ ወደ ሠርጉ ግብዣ ኑ!’ ብላችሁ ንገሩአቸው።


ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ስለሚጠግቡ የተባረኩ ናቸው።


ሕዝቡንም እንደገና ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ሁላችሁም በማስተዋል አዳምጡኝ፤


የሰባውን ወይፈን አምጡና ዕረዱ! እንብላ! እንደሰት!


ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”


ስለዚህ እምነት የሚገኘው የምሥራቹን ቃል ከመስማት ነው፤ የምሥራቹም ቃል የሚገኘው ስለ ክርስቶስ ከሚነገረው ትምህርት ነው።


ነገር ግን ጽድቅ የሚያስገኘውን ሕግ ይከተሉ የነበሩት እስራኤላውያን ሕግን ለመፈጸም ባለመቻላቸው ወደ ጽድቅ አልደረሱም።


“ስለዚህም ዛሬ እኔ የማዛችሁን ሕግ ሁሉ ጠብቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁንም ውደዱ፤ በፍጹም ልባችሁም አገልግሉት።


ባልተለመደ በልዩ ልዩ ዐይነት ትምህርት አትማረኩ፤ ልባችን የመብል ሥነ ሥርዓቶችን በመጠበቅ ሳይሆን በጸጋ ቢጸና መልካም ነው፤ ይህን የምግብ ሥነ ሥርዓት የተከተሉ ሰዎች ምንም አልተጠቀሙም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos