ኢሳይያስ 24:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለጻድቁ ለእርሱ ክብር ይሁን!” የሚል መዝሙር ከዓለም ዳርቻ ይሰማል። እኔ ግን እጅግ በመክሳት ስለ መነመንኩ ወዮልኝ! ከዳተኞች በከዳተኝነታቸው ጸንተዋል፤ ከዳተኛነታቸውም እየባሰ ሄዶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለጻድቁ ክብር ይሁን” የሚል ዝማሬ፣ ከምድር ዳርቻ ሰማን። እኔ ግን፣ “ከሳሁ፤ መነመንሁ፤ ወዮልኝ! ከዳተኞች አሳልፈው ሰጡ፤ ከዳተኞች በክሕደታቸው አሳልፈው ሰጡ” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጻድቁ ክብር ይሁን የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እኔ ግን፦ ከሳሁ፥ ከሳሁ፥ ወዮልኝ! ከሀዲዎች ክህደትን ፈጽመዋል፤ ከሀዲዎች አስከፊ ክህደት ፈጽመዋል አልሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ የጻድቁን ድንቅ ተስፋ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እነርሱ ግን፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ ለሚያፈርሱ ወንጀለኞች ወዮላቸው!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለጻድቁ ክብር ይሁን የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እኔ ግን፦ ከሳሁ፥ ከሳሁ፥ ወዮልኝ! ወንጀለኞች ወንጅለዋል፥ ወንጀለኞች እጅግ ወንጅለዋል አልሁ። |
ስላደረግሃቸው ተአምራት ዓለም በሙሉ በፍርሃት ይዋጣል፤ በአንተ ድንቅ ሥራ ምክንያት ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ የእልልታ ድምፅ ይሰማል።
“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?
ስለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ በግዙፉ ሠራዊቱ ላይ የሚያመነምን በሽታ ይልክበታል፤ በሰውነቱም ውስጥ እንደ እሳት የሚያቃጥል ትኲሳት ይልክበታል።
በዚያን ጊዜ ጌታ በመላው ዓለም ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ከአራቱ ማእዘን ሰብስቦ ያመጣቸው መሆኑን ለመንግሥታት ሁሉ የሚያሳውቅበትን አርማ ከፍ አድርጎ ያቆማል።
አስፈሪ የሆነ ራእይ ተገልጦልኛል፤ ይኸውም አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ከዳተኛው ይከዳል፤ ዘራፊውም ይዘርፋል። የዔላም ሠራዊት ሆይ! አደጋ ለመጣል ውጡ! የሜዶን ሠራዊት ሆይ! ከተሞችን ክበቡ! እግዚአብሔር በባቢሎን ምክንያት የደረሰውን ሥቃይ ሁሉ ያስወግዳል።
አምላክ ሆይ! የምድራችንን ወሰን በየአቅጣጫው በማስፋት መንግሥታችንን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ ሕዝባችንንም አበዛህ፤ ይህም አንተ የምትከብርበት ሆኖአል።
አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል።
ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! በባሕሩ ውስጥ ያሉት ሁሉ፥ የጠረፍ አገሮችና በእነርሱም የሚኖሩ ሁሉ ያመስግኑ!
እኔ የምናገረውን አትሰሙም፤ ለማወቅም አትፈልጉም፤ ከጥንት ጀምሮ ጆሮአችሁ የተደፈነ ነው፤ ይህም የሆነው እናንተ በጣም ከዳተኞች መሆናችሁንና ከተወለዳችሁ ጀምሮ ዐመፀኞች ተብላችሁ መጠራታችሁን ዐውቃለሁ።
እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።
እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው?
ወንድሞችህና የቅርብ ዘመዶችህ ከድተውሃል፤ በአንተ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፤ ስለዚህ በፊትህ ስለ አንተ መልካም ነገር ቢናገሩም አትመናቸው።”
በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጒንጮችዋ ላይ ይወርዳል፤ ከአፍቃሪዎችዋ ሁሉ እርስዋን የሚያጽናና አንድ እንኳ የለም፤ ወዳጆችዋ የነበሩ ሁሉ ከድተዋታል፤ በጠላትነትም ተነሥተውባታል።
እነርሱ ራሳቸው ጣዖት አምላኪዎች ስለ ሆኑ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልተገኙም። ልጆቻቸውም እንደ ጣዖት ልጆች ተቆጥረዋል፤ ስለዚህ በዚህ ወር መባቻ እነርሱም ምድራቸውም አብረው ይጠፋሉ።
እርሱ በእግዚአብሔር ኀይል ተነሥቶ የበግ መንጋውን ያሰማራል፤ ይህንንም የሚያደርገው በግርማዊው በእግዚአብሔር በአምላኩ ስም ነው፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ስለሚሆን እነርሱ ያለ ስጋት ይኖራሉ።
ዐይኖችህ እጅግ የጠሩ ስለ ሆኑ፥ ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ማየት አይስማማህም፤ ታዲያ እነዚህን ዐመፀኞችን እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታቸዋለህ? ክፉዎችስ ከእነርሱ ይበልጥ ደጋግ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠፉ ሲነሡ ስለምን ዝም ትላለህ?
ለምን ይህ ሁሉ ግፍ ሲደርስ እንዳይ አደረግኸኝ? አንተስ ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታለህ? ጥፋትንና ዐመፅን አያለሁ፤ ጠብና ክርክርም ይነሣሉ።
መላእክቱንም ይልካል፤ እነርሱ በአራቱም አቅጣጫ ሄደው ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የሚገኙትን፥ ለእርሱ የተመረጡትን ሰዎች ይሰበስባሉ።
የእግዚአብሔርን አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፥ “ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፤ የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነት ነው፤