Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 24:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ለጻድቁ ክብር ይሁን የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እኔ ግን፦ ከሳሁ፥ ከሳሁ፥ ወዮልኝ! ከሀዲዎች ክህደትን ፈጽመዋል፤ ከሀዲዎች አስከፊ ክህደት ፈጽመዋል አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ለጻድቁ ክብር ይሁን” የሚል ዝማሬ፣ ከምድር ዳርቻ ሰማን። እኔ ግን፣ “ከሳሁ፤ መነመንሁ፤ ወዮልኝ! ከዳተኞች አሳልፈው ሰጡ፤ ከዳተኞች በክሕደታቸው አሳልፈው ሰጡ” አልሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “ለጻድቁ ለእርሱ ክብር ይሁን!” የሚል መዝሙር ከዓለም ዳርቻ ይሰማል። እኔ ግን እጅግ በመክሳት ስለ መነመንኩ ወዮልኝ! ከዳተኞች በከዳተኝነታቸው ጸንተዋል፤ ከዳተኛነታቸውም እየባሰ ሄዶአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ የጻ​ድ​ቁን ድንቅ ተስፋ ከም​ድር ዳርቻ ሰም​ተ​ናል። እነ​ርሱ ግን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ለሚ​ያ​ፈ​ርሱ ወን​ጀ​ለ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው!” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለጻድቁ ክብር ይሁን የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እኔ ግን፦ ከሳሁ፥ ከሳሁ፥ ወዮልኝ! ወንጀለኞች ወንጅለዋል፥ ወንጀለኞች እጅግ ወንጅለዋል አልሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 24:16
41 Referencias Cruzadas  

አስጨናቂ ራእይ ተነገረኝ፤ ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፥ ውጪ! ሜዶን ሆይ፥ ክበቢ፤ ጭንቀቷን ሁሉ አጠፋለሁ።


የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ አታለዋል ይላል ጌታ።


አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፥ አንተም ሳትካድ ክህደትን የምትፈጽም ወዮልህ! ማጥፋትን በተውክ ጊዜ ትጠፋለህ፤ መካድን በተውክ ጊዜ ትካዳለህ።


የእስራኤል ቤት ሆይ! በእውነት ሚስት ባልዋን እንደምታታልል እንዲሁ አታለላችሁኝ ይላል ጌታ።’”


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባርያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


እንዲሁ ጌታ “እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ፤” ብሎ አዞናልና፤ አሉ።


እርሱም መላእክቱን ልኮ ከአራቱ ነፋሳት፥ ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማያት ዳርቻ ምርጦቹን ይሰበስባል።


ክፉ ሥራ ለምን አሳየኸኝ? ድካምንስ ለምን ትመለከታለህ? ጥፋትና ግፍ በፊቴ ነው፤ ጠብና ክርክር ይነሣሉ።


ይህም ሰላም ይሆናል፤ አሦር ወደ ምድራችን ከመጣ፥ ምሽጎቻችንንም ከረገጠ፥ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።


እነርሱ ግን በአዳም ቃል ኪዳንን ተላልፈዋል፤ በዚያም ቦታ እኔን አታለውኛል።


ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና ጌታን አታልለዋል፤ አሁን ደግሞ እነርሱን ከርስታቸው ጋር የወሩ መባቻ ይበላቸዋል።


ቤት። በሌሊት እጅግ ታላቅሳለች፥ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፥ ከውሽሞችዋ ሁሉ የሚያጽናናት የለም፥ ወዳጆችዋ ሁሉ ወነጀሉአት ጠላቶችም ሆኑአት።


ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አታልለውሃልና፥ በኋላህም ጮኸዋልና፤ በመልካምም ቢናገሩህም አትመናቸው።”


ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እንድከብር የአታክልቴን ቡቃያ፥ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘለዓለም ይወርሳሉ።


ጌታ የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፥ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ።


አልሰማህም፥ አላወቅህም፥ ጆሮህ ከጥንት አልተከፈተችም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደሆንህ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ አውቄአለሁና።


በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል፤


ሕዝብን አበዛህ፥ አቤቱ ጌታ፥ ሕዝብን አበዛህ፤ አንተም ተከበርህ፥ የአገሪቱንም ዳርቻ ሁሉ አሰፋህ።


በዚያን ቀን የያዕቆብ ክብር ይደበዝዛል፥ የሰውነቱም ውፍረት ይመነምናል።


ስለዚህ ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በፈረጠሙ ጦረኞቹ ላይ የሚያከሳ በሽታ ይልካል፤ ከክብሩም በታች እንደ ነበልባል የሚንቦገቦግ እሳት ይለኰሳል።


የለመኑትንም ሰጣቸው፥ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።


ለእስራኤል ቤት ያለውን ጽኑ ፍቅርና ታማኝነት አስታወሰ፥ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን አዩ።


ምድር ፍሬዋን ሰጠች፥ እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።


ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።


ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።


ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?


አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?


ከእናንተም መካከል የተረፉት በጠላቶቻቸው ምድር ላይ በኃጢአታቸው ይመነምናሉ፤ በአባቶቻቸውም ኃጢአት ደግሞ እንደ እነርሱ ይመነምናሉ።


የባሕሩን ማጓራት፥ የሞገድንም ጩኸት፥ የአሕዛብንም ማጉረምረም ዝም ታሰኛለህ።


ቃልህን አልጠበቁምና ሰነፎችን አይቼ አዘንሁ።


ለመንግሥታት ምልክትን ያቆማል፤ ከእስራኤልም የተሰደዱትን መልሶ ያመጣቸዋል፤ የተበተኑትን የይሁዳ ሕዝብ፤ ከአራቱ የምድር ማእዘን ይሰበስባል።


ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርሷም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ፥ ለጌታ አዲስ መዝሙር፥ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።


ዐይኖችህ ክፉ እንዳያዩ እጅግ ንጹሐን ናቸው፥ ክፉ ሥራም መመልከት አትችልም፤ አታላዮችን ለምን ትመለከታለህ? ክፉዎቹ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆኑትን ሲውጡ ለምን ዝም ትላለህ?


እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios