Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 58:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኃጢአተኞችን ሲበቀልላቸው በማየታቸው ጻድቃን ደስ ይላቸዋል፤ በክፉዎችም ደም እግሮቻቸውን ይታጠባሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጻድቃን በቀልን ባዩ ጊዜ ደስ ይላቸዋል፤ እግራቸውንም በግፈኞች ደም ይታጠባሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ድስታችሁ የእሾኽን መቀጣጠል ከመስማቱ በፊት፥ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ጠራርጎ ያጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የአ​ም​ላኬ ይቅ​ር​ታው ይድ​ረ​ሰኝ አም​ላኬ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አሳ​የኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 58:10
16 Referencias Cruzadas  

ክፉ ሰዎች ሲቀጡ በማየት ደጋግ ሰዎች ይደሰታሉ፤ ቀጥተኞች እንዲህ እያሉ በእነርሱ ላይ ያፌዛሉ፥


እግሮቼ እንኳ በወተት እስኪታጠቡ ድረስ ብዙ ወተት አገኝ ነበር። የወይራ ዛፎቼም በጭንጫ መሬት ላይ እንኳ ተተክለው እንደ ጐርፍ የሚወርድ ብዙ ዘይት ይሰጡኝ ነበር።


ቅኖች ይህን በማየት ደስ ይላቸዋል፤ ክፉዎች ግን ዐፍረው ዝም ይላሉ።


የእግዚአብሔር ሰዎችም ይህን አይተው ይፈራሉ፤ እንዲህ እያሉ ይሳለቃሉ፤


ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላቸው እርሱንም ከለላ ያድርጉ፤ ልባቸውም ቅን የሆነ ሁሉ ያመስግኑት።


አንተ ደማቸውን ረግጠህ ታልፋለህ፤ ውሾችህም ደም ይልሳሉ።”


ክፉዎች ሲቀጡ በዐይንህ ታያለህ።


ዐውሎ ነፋስ በሚነሣበት ጊዜ ክፉዎች ተጠርገው ይወሰዳሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን ዘወትር ጸንተው ይኖራሉ።


ለጻድቃን፥ ሁሉ ነገር ሲሳካላቸው በከተማው ውስጥ ደስታ ይሆናል። ክፉዎች ሲጠፉ ደግሞ እልልታ ይሆናል።


“ሕዝቦች ሆይ፥ እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋል፤ የሚጠሉትን ቀጥቶ የሕዝቡን ኃጢአት ያስተሰርያል፤ የምድሪቱን ርኲሰት ያነጻል ስለዚህ ከእርሱ ሕዝብ ጋር ደስ ይበላችሁ።”


ከከተማው ውጪ ባለው በወይን መጭመቂያም ተጨመቀ፤ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረስ ልጓም ወደ ላይ ከፍ ያለና ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት የሚደርስ ደም ወጥቶ ፈሰሰ።


ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!


እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህን ሁሉ በዚህ ዐይነት አጥፋ፤ ወዳጆችህ ግን እንደ ንጋት ፀሐይ ይድመቁ። ከዚህ በኋላ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos