Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 52:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ፊት ኀያልነቱን ይገልጣል፤ መላው ዓለምም የእርሱን አዳኝነት ያያል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ፊት፣ የተቀደሰ ክንዱን ይገልጣል፤ በምድር ዳርቻዎች ያሉ ሁሉ፣ የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታ የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፥ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ክን​ዱን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ገል​ጦ​አል፤ በም​ድር ዳርቻ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ሁሉ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን ያያሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፥ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 52:10
27 Referencias Cruzadas  

ለመሆኑ ኀይልህ እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ኀይል የበረታ ነውን? ድምፅህስ እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነውን?


እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ ሰዎች ሁሉ አስታውሰው ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ በዓለም የሚገኙት ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ።


ዓለም በሙሉ የአንተን መንገድ፥ ሕዝቦችም የአንተን አዳኝነት ይወቁ።


በእግዚአብሔር ቅዱስ ተራራ ላይ ምንም ጒዳት አይደርስም፤ ባሕር በውሃ እንደሚሞላ ምድርም እግዚአብሔርን በሚያውቁና በሚያከብሩ ሰዎች ትሞላለች።


ይህም በሚፈጸምበት ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ “እነሆ፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ በእርሱ ስለ ታመንን አድኖናል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ እኛም በእርሱ ታምነናል፤ እርሱ ስለ ታደገን በደስታ ተሞልተን ሐሴት እናደርጋለን!” ይላሉ።


እግዚአብሔር ክቡር ድምፁን እንዲሰሙ ያደርጋል። በኀይለኛ ቊጣው፥ በሚያቃጥል የእሳት ነበልባል፥ በመብረቅ፥ በወጀብና በጠጣር በረዶ የሚወርደው ኀይለኛ ቅጣቱ እንዲታይ ያደርጋል።


እናንተ በሩቅ ያላችሁ የሠራሁትን ስሙ፤ እናንተም በቅርብ ያላችሁ ኀያልነቴን አረጋግጡ።”


በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ክብር ይገለጣል፤ እግዚአብሔር ይህን የተናገረ ስለ ሆነ ሰዎች ሁሉ ይህን በአንድነት ሆነው ያዩታል።”


“ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ ስለሌለ፥ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያላችሁ ሁሉ ወደ እኔ ተመልሳችሁ ደኅንነትን አግኙ።


እንግዲህ ከባቢሎን ወጥታችሁ ሽሹ፤ “እግዚአብሔር አገልጋዩን እስራኤልን አድኖአል” የሚለውን የምሥራች ቃል በደስታ አብሥሩ፤ በየስፍራውም እንዲታወቅ አድርጉ።


እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።


እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።


ሕዝቡም እንዲህ ሲሉ ይመልሳሉ፦ “እኛ የምንናገረውን ማን ያምነናል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?


ተጨቋኞችን የሚረዳ አንድ ሰው እንኳ አለመገኘቱ አስገረመው፤ ስለዚህ እነርሱን ለማዳን በኀይሉ ተጠቅሞ ድልን እንዲጐናጸፉ አደረጋቸው።


የሚሰጣት ፍርድ እንደ ንጋት እስኪፈነጥቅና መዳንዋም እንደሚነድ ችቦ እስኪበራ ድረስ፥ ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ ስለ ኢየሩሳሌምም ከማሰብ አላርፍም።


ዙሪያዬን በተመለከትኩ ጊዜ የሚረዳ ማንም አልነበረም። ደጋፊ ባለመኖሩ ተደነቅሁ፤ ስለዚህ በኀይለኛ ቊጣዬ አማካይነት እኔው ራሴ ድልን አመጣሁ።


እርሱ በእግዚአብሔር ኀይል ተነሥቶ የበግ መንጋውን ያሰማራል፤ ይህንንም የሚያደርገው በግርማዊው በእግዚአብሔር በአምላኩ ስም ነው፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ስለሚሆን እነርሱ ያለ ስጋት ይኖራሉ።


ማዳንህን በዐይኔ አይቻለሁ፤


ሰውም ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ!’ ”


ይህንንም የምናደርገው ጌታ፦ ‘መዳንን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንድታመጣ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ’ በማለት ስላዘዘን ነው።”


በዚህም ምክንያት በምድር ላይ የሚኖር ሕዝብ ሁሉ የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ እንደ ሆነ ይገነዘባል፤ እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔርን ለዘለዓለም ታከብራላችሁ።”


ከዚህ በኋላ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ፥ ነገድ፥ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን ለሚናገሩና ለተለያዩ ወገኖች ሁሉ ለማብሠር ዘለዓለማዊውን ወንጌል የያዘ ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ።


ጌታ ሆይ! አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ፤ የእውነት ፍርድህ ስለ ተገለጠ፥ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos