158 ቃልህን ስለማይጠብቁ፥ ከሐዲዎችን አይቼ ተጸየፍኳቸው።
158 ቃልህን አይጠብቁምና፣ ከዳተኞችን አይቼ አርቃቸዋለሁ።
158 ቃልህን አልጠበቁምና ሰነፎችን አይቼ አዘንሁ።
ሰዎች ሕግህን ስለ ጣሱ እንባዬ እንደ ወንዝ ውሃ ይፈስሳል።
ክፉ ሰዎች ሕግህን ሲተላለፉ በማየቴ በብርቱ ተቈጣሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! የሚጠሉህን እጅግ እጠላቸዋለሁ! በአንተ ላይ የሚያምፁትንም እጅግ እጸየፋቸዋለሁ!
“በመላዋ ኢየሩሳሌም ከተማ ተዘዋወር፤ በከተማይቱ ከተፈጸመውም አጸያፊና አሳፋሪ ነገር የተነሣ በመሠቀቅ ባዘኑት ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት አድርግባቸው!” አለው።
ኢየሱስም ስለ ልባቸው ድንዛዜ አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በቊጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት።