መዝሙር 67 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምየምስጋና መዝሙር 1 እግዚአብሔር ይማረን፥ ይባርከንም፤ የፊቱ ብርሃን በላያችን ይብራ። 2 ዓለም በሙሉ የአንተን መንገድ፥ ሕዝቦችም የአንተን አዳኝነት ይወቁ። 3 አምላክ ሆይ፥ ሕዝቦች ያመስግኑህ፤ ሕዝቦች ሁሉ ያመስግኑህ። 4 ለሕዝቦች በቅንነት ስለምትፈርድና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ስለምትመራ፤ መንግሥታት ደስ ይበላቸው፤ በሐሤትም እልል ይበሉ። 5 አምላክ ሆይ! ሕዝቦች ያመስግኑህ፤ ሕዝቦች ሁሉ ያመስግኑህ። 6 በዚያን ጊዜ ምድር ፍሬ ትሰጣለች፤ እግዚአብሔር አምላካችን ይባርከናል። 7 እግዚአብሔር ስለሚባርከንም በምድር ዳርቻ ያሉ ሁሉ ይፈሩታል። |