በተጨማሪም የካህናት መሪዎችና ሕዝቡ ጣዖቶችን በማምለክ በዙሪያቸው የሚገኙትን ሕዝቦች መጥፎ ምሳሌነት ተከተሉ፤ እግዚአብሔር ራሱ የቀደሰውን ቤተ መቅደስም አረከሱ፤
ኢሳይያስ 1:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ግብረ አበሮች ሆኑ፤ እያንዳንዱ ሁልጊዜ ገጸ በረከትና ጉቦ ይቀበላል፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት አይጠብቁም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ አይሰሙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጕቦን ይወድዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆችሽ አመጸኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፥ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፥ ዋጋም ለማግኘት ይሮጣሉ፥ ለድሀ አደጉ አይፈርዱም፥ የመበለቲቱም ሙግት ወደ እነርሱ አይደርስም። |
በተጨማሪም የካህናት መሪዎችና ሕዝቡ ጣዖቶችን በማምለክ በዙሪያቸው የሚገኙትን ሕዝቦች መጥፎ ምሳሌነት ተከተሉ፤ እግዚአብሔር ራሱ የቀደሰውን ቤተ መቅደስም አረከሱ፤
መልካም ማድረግንም ተማሩ፤ ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ የተጨቈኑትን ታደጉ፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት ጠብቁ፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ ስሙ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስቲ ኑና እንወያይ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ቢቀላ እኔ አጥቤ እንደ በረዶ ይጸዳል፤ እንደ ደም የቀላ ቢሆን እንደ ባዘቶ ይነጣል።
ስለዚህ የሕዝቡን መሪዎችና አማካሪዎች ወደ ፍርድ አቅርቦ እንዲህ ይላቸዋል፦ “የወይኑን አትክልት ቦታ ዘረፋችሁ፤ ከድኾች በተዘረፈው ሀብትም ቤታችሁን ሞላችሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዐመፀኞች ለሆኑ ልጆች ወዮላቸው! እኔ ባላወጣሁላቸው ዕቅድ መመራት ይፈልጋሉ፤ ከእኔም ፈቃድ ውጪ የቃል ኪዳን ውል በመፈጸም በኃጢአት ላይ ኃጢአት ይጨምራሉ።
በእውነትና በትክክል የሚናገሩ፥ በግፍ የሚገኝን ትርፍ የሚጸየፉ፥ ጉቦን ከመቀበል ይልቅ የሚያስወግዱ፥ ስለ ነፍስ ግድያ መስማት የማይፈልጉና፥ ክፉ ነገርን ከማየት ዐይኖቻቸውን የሚጨፍኑ፥
የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ፥ የእነርሱ ነገሥታት፥ ባለሥልጣኖቻቸው፥ የእነርሱ ካህናትና ነቢያት በሚያደርጉአቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ ቊጣዬን አነሣሥተዋል።
እንግዲህ በሥልጣን ላይ ወዳሉት ገዢዎች ሄጄ፥ ከእነርሱ ጋር እነጋገራለሁ፤ በእርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉ፤” ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀዋል፤ ለእርሱም መታዘዝ እምቢ ብለዋል።
ሕዝቡ ብዙ ጊዜ ዐምፀው እግዚአብሔርን ትተዋል፤ ስለዚህ ጠላቶቻቸው እንደ ዱር አንበሶች ወይም እንደ በረሓ ተኲላዎች አደጋ ይጥሉባቸዋል፤ እነዚያም ጠላቶች በከተሞቹ ላይ ሸምቀው ከዚያ የሚወጡትን ሰዎች ሁሉ እንደ ነብር ሆነው ይቦጫጭቁአቸዋል።
“የሰው ልጅ ሆይ! አንተ የምትኖረው ዐመፀኞች በሆኑ ሕዝብ መካከል ነው፤ እነርሱ ዐመፀኞች ከመሆናቸው የተነሣ ዐይን እያላቸው አያዩም፤ ጆሮም እያላቸው አይሰሙም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ መሪዎች የእስራኤልን ድንበር እንደሚያፈርሱ ሰዎች ሆነዋል፤ ስለዚህ እኔ ቊጣዬን እንደ ጐርፍ ውሃ አወርድባቸዋለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ገና በጌልገላ ሳሉ ክፉ ሥራቸው ተገለጠ፤ እኔም በዚያ የእነርሱን ሥራ መጥላት ጀመርኩ፤ ስለ ሠሩትም ክፉ ሥራ ከሰጠኋቸው ምድር አስወጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለእነርሱ ፍቅር አላሳያቸውም፤ መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ሆነዋል።
በደላችሁ ምን ያኽል እንደ በዛና ኃጢአታችሁም ምን ያኽል ከባድ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ደጋግ ሰዎችን ታስጨንቃላችሁ፤ ጉቦ እየተቀበላችሁ በየፍርድ አደባባዩ የምስኪኖችን ፍትሕ ታጣምማላችሁ።
የከተማይቱም ሹማምንት የሚፈርዱት በጉቦ ነው፤ ካህናቱ ያለ ዋጋ አያስተምሩም፤ ነቢያቱም ያለ ገንዘብ ትንቢት አይናገሩም፤ ይህም ሁሉ ሆኖ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይመጣብንም” በማለት በእግዚአብሔር ይመካሉ።
እጆቻቸው ክፉ ነገርን ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ባለ ሥልጣኑና ዳኛው ጉቦ ይጠይቃሉ፤ ኀይለኛ ፍላጎቱን በግዴታ ተግባራዊ ያስደርጋል፤ በዚህም ዐይነት ሁሉም ፍርድን ያጣምማሉ።
በመካከላችሁ የሚኖሩትን ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ አባትና እናት የሌላቸውን ድኻ አደጎች፥ መጻተኞችንና ችግረኞችን አትጨቊኑ፤ እርስ በርሳችሁ አንዳችሁ ሌላውን ለመጒዳት አታስቡ።’
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።
በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ያልረከሰ ሃይማኖት “አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች፥ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳት፥ ራስንም ከዓለም ርኲሰት መጠበቅ ነው።”
ነገር ግን የአባታቸውን መልካም አርአያነት አልተከተሉም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ የገንዘብ ጥቅም ፈላጊዎች ሆነው ጉቦ እየተቀበሉ ፍርድን ያጣምሙ ነበር።