Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሚልክያስ 3:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ስለዚህ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመተተኞች፣ በአመንዝራዎች፣ በሐሰት በሚምሉ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ በሚከለክሉ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቍኑ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ፣ እኔንም በማይፈሩት ላይ እመሰክርባቸው ዘንድ እፈጥናለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፥ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ሚልክያስ 3:5
63 Referencias Cruzadas  

ጋብቻ በሁሉ ዘንድ የተከበረ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን እግዚአብሔር ስለሚፈርድባቸው ባልና ሚስት ታማኝነትን በማጒደል ጋብቻን አያርክሱ።


“ ‘የእኔን የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሰው እግዚአብሔር ሳይቀጣው አይቀርም።


ይሁን እንጂ በእርሻችሁ ሲያጭዱ ለዋሉት ሠራተኞች ዋጋቸውን ስላልከፈላችሁ እነሆ፥ የተቃውሞ ጩኸታቸው ይሰማል፤ የመከር ሰብሳቢዎቹንም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ሰምቶአል።


“ስለምን መሥዋዕታችንን አይቀበልም?” ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ እግዚአብሔር መሥዋዕታችሁን የማይቀበለው የቃል ኪዳን ጓደኞቻችሁ ለሆኑት ለወጣትነት ሚስቶቻችሁ ታማኝነታችሁን ስላፈረሳችሁ ነው፤ በእናንተም መካከል እግዚአብሔር ምስክር ነበር።


“ ‘መብት በመግፈፍ መጻተኞችን፥ ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆችንና ባሎቻቸው የሞቱባቸው መበለቶችን የሚያንገላታ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።


እንደ ውሻ የሚልከፈከፉ፥ አስማተኞች፥ አመንዝሮች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸትን የሚወዱና በሐሰት መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ከከተማይቱ ውጪ ይሆናሉ።


ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


“ወንድ ወይም ሴት የሙታን መናፍስት ጠሪዎች ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ይገደሉ፤ በድንጋይ ተወግረው ይገደሉ፤ በሞት የሚቀጡትም በራሳቸው በደል ነው።”


“ማንም ሰው ምክር ለመጠየቅ ወደ ሙታን መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች ቢሄድ በዚያ ሰው ላይ ቊጣዬን አወርዳለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ፤


“በጐረቤትህ ላይ ግፍ አትሥራ፤ ወይም ንብረቱን አትቀማው፤ ቀጥረህ የምታሠራውን ሰው ደመወዝ ለአንድ ሌሊት እንኳ በአንተ ዘንድ አይደር።


በቃላችሁ እግዚአብሔርን አሰልችታችሁታል፤ “እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው?” ትላላችሁ፤ እርሱን ያሰለቻችሁት፦ “ክፉ አድራጊ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፤ እግዚአብሔርንም ያስደስተዋል” በማለት ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” ብላችሁ በመጠየቅ ነው።


ዕድል ፈንታቸውም ይህ የሚሆንበት ምክንያት አሠቃቂ ኃጢአት በመሥራታቸው ነው፤ ይኸውም ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ጋር አመንዝረዋል፤ እኔም ያላዘዝኳቸውን የሐሰት ቃል በስሜ ተናግረዋል፤ ይህም እኔ ያልፈቀድኩት ነገር ነው፤ ያደረጉትን ሁሉ ስለማውቅባቸው በእነርሱ ላይ እመሰክርባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”


በፍቅርና በእምነት ኃጢአት ይሰረያል፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ሰው ከክፉ ነገር ይርቃል።


ክፉ ነገርን መጥላት እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ እኔ ትዕቢትንና ዕብሪትን እጠላለሁ፤ ክፉ መንገድንና ጠማማ ንግግርን አልወድም


እግዚአብሔር በምድር ላይ ሊፈርድ ስለሚመጣ በፊቱ ይዘምሩ፤ እርሱም በዓለም ላይ በጽድቅ፥ በሕዝቦች ላይ በትክክል ይፈርዳል።


አንዳንድ ሰዎች “መልካም ነገር እንድናገኝ ክፉ ነገር እናድርግ” እያልኩ የማስተምር አስመስለው ይከሱኛል፤ ስለዚህ እንዲህ ባሉት ላይ የሚፈረድባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው።


እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁም ይህን ስሙ! በምድር ላይ የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ! ጌታ እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ ሆኖ ያጋልጣችኋል።


እርሱም በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፥ በሰዎች ላይ በእውነተኛነቱ ይፈርዳል።


ሕዝቤ ሆይ! የማስጠንቀቂያ ንግግሬን ስማ! እስራኤል ሆይ! ብታዳምጡኝ ምንኛ መልካም ነበር!


ከእኔ በፊት የሕዝብ ገዢ ሆኖ የተሾመው ሁሉ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመሆን፥ በየቀኑ ለምግብና ለመጠጥ የሚሆን አርባ ብር ያስከፍላቸው ነበር፤ የገዢዎቹም አገልጋዮች እንኳ በሕዝቡ ላይ ሠልጥነውባቸው ይጨቊኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንደዚያ አላደረግሁም።


“መጻተኞችና ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ልጆች ፍትሕ አትከልክላቸው፤ ስለ ብድርም መያዣ አድርገህ ባል የሞተባትን ሴት ልብስ አትውሰድ።


አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ቢያመነዝር፤ አመንዝራውና አመንዝራይቱ ሁለቱም በሞት ይቀጡ፤


በተጨማሪ ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መርጠህ በሕዝቡ ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርገህ ሹም። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ እምነት የሚጣልባቸውና በጉቦም የማይደለሉ ሰዎች መሆን አለባቸው።


አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን በመፍራት የግብጽ ንጉሥ እንዳዘዛቸው አላደረጉም፤ ወንዶችንም ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ተዉአቸው።


በሦስተኛው ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው ስለ ሆንኩ እንዲህ ብታደርጉ ሕይወታችሁን ታድናላችሁ፤


ወንድሞቼ ሆይ! ከሁሉም በላይ በሰማይ ወይም በምድር ወይም በሌላ በምንም ነገር አትማሉ፤ ንግግራችሁ አዎ ከሆነ በእውነት አዎ ይሁን፤ አይደለም ከሆነም በእውነት አይደለም ይሁን፤ እንዲህ ካልሆነ ግን ይፈረድባችኋል።


በዚህ ነገር ማንም ሰው አይተላለፍ፤ ሌላ አማኝን አይበድል፤ ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉትን ጌታ ይቀጣቸዋል።


ሌላው ወንጀለኛ ግን እንዲህ ብሎ ገሠጸው፦ “አንተ በተመሳሳይ ፍርድ ላይ እያለህ እግዚአብሔርን አትፈራምን?


ክፉ ሰው ሁልጊዜ በልቡ ክፋትን ያስባል፤ እግዚአብሔርን ከቶ አይፈራም፤ አያከብረውምም።


አብርሃምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘እዚህ ቦታ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የለም’ ብዬ በማሰብ ‘ሚስቴን ለመውሰድ በመፈለግ ይገድሉኛል’ ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው፤


ማንም ከመካከልህ ወንድ ልጁን፥ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ አይኑር፤ ወይም አስማተኛ፥ ሟርተኛ፥ ጠንቋይ፥ መተተኛ አይሁን።


ከአስማተኞች፥ ከአመንዝራዎችና ከዘማውያን የማትሻሉ እናንተ ወደ እዚህ ቅረቡ!


እናንተ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁ በስሜ ትምላላችሁ፤ ነገር ግን የምትምሉት በሐሰት ነው።”


“ታዲያ እኔ እግዚአብሔር ስለዚህ ሁሉ ነገር ልቀጣቸው አይገባኝምን? እንደዚህ ያለውንስ ሕዝብ መበቀል አያስፈልገኝምን?


ምድሪቱ እግዚአብሔርን በተዉ አመንዝሮች ተሞልታለች፤ ነቢያቱ ኀይላቸውን ያለ አግባቡ ይጠቀማሉ፤ የክፋትንም መንገድ ይከተላሉ፤ ከእግዚአብሔር ርግማን የተነሣ፥ ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ መስኮችም ደርቀዋል።


ነቢያታችሁንና በጥንቈላ፥ በመተት፥ ወይም የሙታን መናፍስትን በመሳብና ሕልም በማየት ወደ ፊት የሚሆነውን ነገር ሁሉ እናውቃለን የሚሉትን ሁሉ አትስሙአቸው፤ እነርሱ ሁሉ የሚመክሩአችሁ ለባቢሎን ንጉሥ አትገዙም ብለው ነው፤


እነርሱ ለእናንተ የሚናገሩት ትንቢት የሐሰት ትንቢት ነው፤ ከትውልድ አገራችሁ ወደ ሩቅ አገር ትወሰዳላችሁ፤ እኔም ስለማሳድዳችሁ ትጠፋላችሁ።


ከዚህም በኋላ እነርሱ እንዲህ አሉኝ “አምላክህ እግዚአብሔር በአንተ አማካይነት የሚሰጠንን ትእዛዝ ሁሉ በመፈጸም ለቃሉ ታዛዦች ሆነን ባንገኝ፥ እርሱ ራሱ በእኛ ላይ እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁንብን!


እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! አንተ ከጥንት ጀምሮ የነበርክ ቅዱስ ነህ፤ አንተ ስለምትጠብቀን አንሞትም፥ እነርሱ ፍርድህን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መድበሃቸዋል፤ አምባችን ሆይ! እኛን እንዲቀጡ ለእነርሱ ሥልጣን ሰጥተሃቸዋል።


እኔም “ብትፈቅዱ ደመወዜን ስጡኝ፤ ባትፈቅዱ ተዉት” አልኳቸው፤ እነርሱም የአገልግሎቴን ዋጋ ሠላሳ ብር ሰጡኝ።


“የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን ሁሉ ሳይቀጣው አያልፍም።


“ለእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ለሌላ ለማንኛውም አምላክ መሥዋዕት የሚያቀርብ በሞት ይቀጣ።


ነጻ በምታወጣው ጊዜ ባዶ እጁን አትስደደው፤


እነርሱም በጥላ ሥር ለማረፍ እንደሚፈልጉ አገልጋዮችና ደመወዛቸውን ለመቀበል እንደሚጠባበቁ ሙያተኞች አይደሉምን?


ይህ ኃጢአት እንደ እሳት አቃጥሎ የሚያጠፋ ስለ ሆነ እኔ ይህን ብሠራ ኖሮ ሀብቴን ሁሉ ባወደመው ነበር።


የሠራዊት አምላክ ካህናቱን እንዲህ ይላቸዋል፦ “ልጅ አባቱን፥ አገልጋይም አሳዳሪ ጌታውን ያከብራል፤ እነሆ፥ እኔ አባታችሁ ከሆንኩ ለምን አታከብሩኝም? ጌታችሁም ከሆንኩ ለምን ክብር አትሰጡኝም? እናንተ የእኔን ስም ንቃችኋል፤ ነገር ግን ‘ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios